አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30913 — TG.ME

አጋቾችንና ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️
በደብረ ብርሃን ከተማ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የፀጥታ መዋቅር ህገወጥ ተግባራትን በመከታተል አጋቾችንና ዘራፊዎችን ከነ ማስረጃዎቻቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገለጸ።

ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት አንድ ልጅ በማገት 5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን፣ ከልጅ ቤተሰብ ጋር በመደራደር 3 ሚሊዮን ብር መቀበላቸው ታውቋል።

የክፍለ ከተማው የፀጥታ መዋቅር በወቅቱ የተገኘውን መረጃ ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ መረጃ በማሰባሰብና ክትትል በማድረግ ቆይቶ፣ ተጠርጣሪዎቹን ከነ ማስረጃዎቻቸው በቁጥጥር ስር አውሏል።

በእርምጃውም በርካታ የጦር መሳሪያዎች፣ የሞባይል ስልኮች፣የተለያዩ የባንክ አካውንት ደብተሮችና የተለያዩ መጠን ያላቸው ጥሬ ገንዘቦች መያዛቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8
August 29, 2026 1.6K 1