አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30853 — TG.ME

በኩዌት ኢትዮጵያዊት ሴት በባሏ አሰቃቂ ግድያ ተፈጸመባት

እንደ ኩዌት ታይምስ ዘገባ ከሆነ ​በኩዌት ጃህራ ግዛት ውስጥ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት በገዛ ኢትዮጵያዊ ባለቤቷ በቢላዋ ሶስት ቦታ ተወግታ ህይወቷ አልፏል።

​ተጠርጣሪው ባለቤት ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ከአካባቢው መሰወሩን አቃቤ ህግ እና የወንጀል ምርመራ ቡድን ባደረጉት የመጀመሪያ ደረጃ ማረጋገጫ ታውቋል።

ዘገባው እንደሚያመለክተው የፖሊስ እና የአምቡላንስ ሰራተኞች ጥቆማው እንደደረሳቸው ወዲያውኑ ቦታው ላይ ቢደርሱም የሴቲቱን ህይወት ማዳን አልተቻለም።

​የአስከሬን ምርመራ ለማካሄድ እና የሟቿን አካል ለማንሳት አቃቤ ህግ እና የፎረንሲክ ባለሙያዎች በቦታው ተገኝተዋል።

የአካባቢው ፖሊስ የድርጊቱን መንስኤ ለማወቅ እና ከአካባቢው ያመለከተውን ተጠርጣሪ ባለቤት አድኖ ለመያዝ ሰፊ የምርመራ ስራ እየሰራ ይገኛል።

የወንጀሉ አሰቃቂነት በቦታው በነበሩ ነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ ድንጋጤን ፈጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13😢13👍4
August 25, 2026 4.6K 5