አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30840 — TG.ME

የንግድ ባንክ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ለወንዶች ያደሉ መሆናቸውን ዓለም ባንክ አረጋገጠ

በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በሥራ ዕድገትና በደመወዝ ክፍያ ረገድ ለወንዶች ያደላ አሠራር መከተሉን የዓለም ባንክ አሳወቀ። ባንኩ ከ50 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን፣ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የባንክ ሠራተኞች አንድ ሦስተኛውን ይይዛል። ሆኖም በውስጡ ያለው የሥራ ድልድል ፍትሐዊ እንዳልሆነ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በባንኩ ዘርፍ በብዛት ሴቶች ቢቀጠሩም፣ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎችን መያዝ ላይ ግን ትልቅ ችግር አለ። የዓለም ባንክ ጥናት እንደሚያሳየው፤  በንግድ ባንክ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ክፍያ የሚከፈላቸው ሲሆን፤ እንደ ኃላፊ ወይም ተቆጣጣሪ ያሉ የሥራ መደቦችን የማግኘት ዕድላቸውም እጅግ ጠባብ ነው።

ይህ በፆታ መካከል የሚታየው ልዩነት በትምህርት፣ በሥራ ልምድ ወይም በብቃት እጥረት የመጣ አይደለም። ባንኩ መደበኛ ደንቦች ቢኖሩትም፣ ሴቶች ከወንዶች ባነሰ ፍጥነት እንዲያድጉ የሚያደርግ  አሠራር መኖሩን ሪፖርቱ አትቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪8❤6👍6🤣4💯1
August 24, 2026 5.5K 5