ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ብን ሙሐመድ አስስልጢ - ሐፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- እወቅ - አሏህ ይምራህ… — ጅብሪል ሱልጣን & ሙሀመድ ሰልማን — TG.ME

🔷 ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ብን ሙሐመድ አስስልጢ - ሐፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :-

እወቅ - አሏህ ይምራህ :

"የፈጠራና የዝንባሌ ባለቤቶች የርዕዮተ አለም አራማጆቻቸውና የታላላቅ መሪዎቻቸውን የፈጠራና የሸሪዓ ጥሰቶች እንደቀላል ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ።

ታይቶ በቀላል የሚታለፍ - ማግለልን ፣ መተውን እና ከዚያ ነገር መራቅን የማያስከትል ተራ ስህተት አድርገው ይቆጥሩታል።

ሰይድ ቁጥብ ከኢስላም ከሚያስወጡ የሸሪዓ ጥሰቶችና በርካታ ፈጠራዎች ላይ የወደቀ ግለሰብ ነው። 

ይህ ከመሆኑ ጋር ቁጥብዮች ፣ ኢኽዋኖችና ሌሎች አንጃዎች እነዚህን ጥሰቶች  በከፍተኛ ደግነት እና ገርነት ሲያስተናግዷት ትመለከታለህ።

ለሰይድ ቁጥብ ቀዝቃዛ ይቅርታ ሲጠይቁ ፤ (እርሱን ለማዳን) ማንኛውንም አይነት ሰበብ ሲፈልጉ ፣ ከእርሱ ላይ  ሲከላከሉና ማህበረሰቡ እርሱን እንዲከተል ፣ በእርሱ ጎዳና  እንዲጓዝ ሲቀሰቅሱ ታስተውላለህ።

ሰይድ ቁጥብ ለኢስላምና ለህዝቦቹ ከሚከላከሉ የተሀድሶ አራማጆች መካከል አንዱ አድርገው ይቆጥሩታል። በእርግጥም ፍቅር ያውራል ፣ ያደነዝዛል።

አሏህ እንዲህ ብሏል:-

أَفَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَٰهَهُ هَوَاهُ وَأَضَلَّهُ اللَّهُ عَلَىٰ عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمْعِهِ وَقَلْبِهِ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِ غِشَاوَةً فَمَن يَهْدِيهِ مِن بَعْدِ اللَّهِ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

"ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አሏህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን ፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን!? ታዲያ ከአሏህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሰጹምን?"

(ጃሲያ :23)


في رسالته : الفصل المبين في دحض شبهات وتلبيسات محمد حامي الدين  ص ١

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة
September 9, 2026 294 4