በመርካቶ ቀበሌ 22 ነዋሪ የነበሩ ሁለት የአንድ ሰፈር ወጣቶች በትላንትናው ዕለት በፑል ቤት የእግር ኳስ…

በመርካቶ ቀበሌ 22 ነዋሪ የነበሩ ሁለት የአንድ ሰፈር ወጣቶች በትላንትናው ዕለት በፑል ቤት የእግር ኳስ ጨዋታን ተመልክተው በሚወጡበት ወቅት በተፈጠረ ንትርክ አንደኛው ሕይወቱ ማለፉ ተገለጸ።

ክስተቱ የተከሰተው ማንችስተር ዩናይትድ በትላንትናው ዕለት ያደረገውን ጨዋታ 4 ለ 0 መሸነፉን ተከትሎ በሁለቱ መካከል የቃላት ልውውጥና መበሻሸቅ ተፈጥሮ እንደነበር ተመላክቷል። በዚህም መሠረት የማንችስተር ደጋፊ የነበረው ሞላ የተባለ ግለሰብ በሊቨርፑል ደጋፊ በነበረው አብድረዛቅ (በሰፈሩ ልጆች ዘንድ «ጭሬ» በመባል በሚታወቀው ወጣት) ላይ ጥቃት ማድረሱ ተነግሯል። ከድርጊቱ በኋላም ግለሰቡ እጁን ለፖሊስ መስጠቱ ተሰምቷል።

ትክክለኛ ስሙ አብድረዛቅ ሲሆን በሰፈሩ ልጆች ዘንድ «ጭሬ» በሚል መጠሪያ ይታወቅ የነበረው ወጣት ሕይወት ካለፈ በኋላ አስከሬኑ ከመርካቶ ተነስቶ በእናቱ መኖሪያ ወደሚገኝበት ሰንዳፋ መሸኘቱ ተጠቁሟል።

ለመዝናናትና ጭንቀትን ለማርገብ የሚታይ የእግር ኳስ ጨዋታ ወደ ዘላቂ ጸጸትና የሰው ሕይወት መጥፋት ሲያመራ ማየት እጅግ ያሳዝናል። በተለይም አብረው ባደጉ የአንድ ሰፈር ወጣቶች መካከል በስፖርታዊ ፉክክር ሳቢያ እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ክስተት መፈጠሩ በእጅጉ ያሳስባል።

መረጃው የጉርሻ ፔጅ ነው
👍1
November 23, 2026 63 1
በመርካቶ ቀበሌ 22 ነዋሪ የነበሩ ሁለት የአንድ ሰፈር ወጣቶች በትላንትናው ዕለት በፑል ቤት የእግር ኳስ… — Zedo News — TG.ME