በ61 ዳቦ አምራቾች ላይ እርምጃ ተወሰደ‼
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በ188 ዳቦ ቤቶች ላይ ባደረገው ቁጥጥር፣ የንግድ ህጉን በተላለፉ 61 አምራቾች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አሳወቀ።
እርምጃው የተወሰደው የ70 ግራም ዳቦ ከ13 ብር በላይ በመሸጥ፣ ከመጠን በታች በማምረትና የዋጋ ዝርዝር ባለመለጠፍ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው።
ቢሮው የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ፣ ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ ተግባራትን ሲመለከት በ8588 ነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቁም ጥሪ አቅርቧል።(አሐዱ)
2

