ኢራናዊቷ ዘፋኝ ሂጃብ ሳታደርግ በኦንላይን
ኮንሰርት በማቅረቧ 74 ጅራፍ ተቀጣች
የኢራን ባለሥልጣናት ዘፋኝ ፓራስቱ አህመዲን እና አራት የሥራ ባልደረቦቿን አስገዳጅ የሆነውን ሂጃብ ሳትለብስ በኢንተርኔት (ኦንላይን) የሙዚቃ ዝግጅት በማቅረቧ የተፈረደባቸውን የ74 ግርፋት ቅጣት ሰኞ ዕለት እንደፈጸሙባቸው ጠበቃቸው ተናገሩ።
ጠበቃ ሙስጠፋ ኒሊ ለኢራኑ 'ኤምቴዳድ' ዜና አውታር እንደገለጹት፣ አህመዲ፣ ሶሄይል ፋጊህ-ናሲሪ፣ አሚን ታሄሪ፣ አሚራሊ ፒርኒያ እና ሞህሰን ላሽካሪ በቆም ከተማ በሚገኘው የዐቃቤ ሕግ ቢሮ ቀርበው ቅጣቱ ተፈጽሞባቸዋል።
ክሱ የተመሠረተው አህመዲ በከተማዋ በሚገኝ አንድ ታሪካዊ ቦታ ውስጥ በቀጥታ ቀርጻ በታኅሣሥ 2024 በዩቲዩብ ቻናሏ ላይ በለቀቀችው የሙዚቃ ኮንሰርት ምክንያት ነው።
ፍርድ ቤቱ አምስቱንም ሰዎች «ከሥነ-ምግባር ውጭ የሆነ ነገር በኢንተርኔት ላይ አዘጋጅተው አሰራጭተዋል» በሚል ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
በዚህም ምክንያት እያንዳንዳቸው 74 ጅራፍ እንዲገረፉ፣ ለሁለት ዓመት ምንም ዓይነት የሙዚቃም ሆነ የኪነ-ጥበብ ሥራ እንዳይሠሩ እንዲሁም ለሁለት ዓመት ከሀገር እንዳይወጡ ተወስኖባቸዋል።

November 23, 2026 152