የድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት የቀብር ሥነ-ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ
ባለፉት ሁለት ቀናት በድንገተኛ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የታዋቂውና ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት የቀብር ሥነ-ሥርዓት፣ ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጥልቅ ሐዘንና በእንባ ተፈጸመ።
በሙዚቃ ሥራዎቹና በድምፁ በበርካታ አድናቂዎቹ ልብ ውስጥ ሕያው ትዝታን ያተረፈው ሚኪያስ ቸርነት፣ ባልታሰበና ድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ማለፉ ቤተሰቦቹን፣ የሙዚቃውን ማኅበረሰብ እንዲሁም መላውን ወዳጅና አድናቂ በእጅጉ አሳዝኗል።
በተለይም የአራት ልጆች አባት የነበረው የድምፃዊው ድንገተኛ ሕልፈት፣ ሐዘኑን ይበልጥ ከባድ፣ መራርና ልብ የሚሰብር አድርጎታል።
በዚህ እጅግ አሳዛኝና መሪር የሐዘን ሰዓት ጉርሻ ፔጅ ለአራቱ ልጆቹ፣ ለመላው ቤተሰቡ፣ ለቅርብ ወዳጆቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ በሙሉ ከልብ የመነጨ መጽናናትን በድጋሚ ይመኛል።
ደኅና ሰንበት ሚኪያችን💔

November 23, 2026 71