ኢሕአፓ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመናን ላይ ያነጣጠሩ የተደራጁ ጥቃቶች በአስቸኳይ…

ኢሕአፓ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመናን ላይ ያነጣጠሩ የተደራጁ ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠየቀ

​የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በእምነቱ ተከታዮችና በአገሪቱ ታሪካዊ ማንነት ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የተደራጁ ጥቃቶችንና የጥላቻ ንግግሮችን በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታወቀ።

​ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፣ እነዚህ በቤተ ክርስቲያኒቱና በምዕመናን ላይ ያነጣጠሩ የመከፋፈልና ታሪክን የማዛባት ድርጊቶች ከተራ የአመለካከት ልዩነት ያለፉ ከባድ ሥጋቶች መሆናቸውን ገልጿል።

​በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተፈጸሙ ላሉ ግድያዎችና ማሳደዶች መንስኤ እየሆኑ የመጡ መሰል ድርጊቶችና ዛቻዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ኢሕአፓ በመግለጫው አሳስቧል።
November 22, 2026 218