የ2019 ዓ.ም. የኢሬቻ በዓል በዱባይ በድምቀት ተከበረ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ዱባይ ከተማ የ2019…

የ2019 ዓ.ም. የኢሬቻ በዓል በዱባይ በድምቀት ተከበረ

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ዱባይ ከተማ የ2019 ዓ.ም. የኢሬቻ በዓል «ኢሬቻ ለአገራዊ መግባባት» በሚል መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

በዚህ ባህላዊ እና ሕዝባዊ የምስጋና ሥነ-ሥርዓት ላይ የአባ ገዳና የሀደ ሲንቄ ተወካዮችን ጨምሮ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ቆንሱል ጄኔራል አምባሳደር ዘሪሁን መገርሳ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም በአቡዳቢና በዱባይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ባልደረቦች፣ የአቡዳቢ እና የዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማኅበር አመራሮች እንዲሁም በኤምሬቶች የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በበዓሉ ላይ ተሳትፈዋል።

©️በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ቆንሱል ጄኔራል
November 22, 2026 234