ከመኝታ ክፍሌ ወጥቼ ግቢ ውስጥ በቀርቀሃ ከተሰራ አግዳሚ ወንበር ላይ አረፍ አልኩ። ከፊቴ ተንጧሎ በሚታየው… — yero's reflections/ የየሮ ንጽረቶች — TG.ME

ከመኝታ ክፍሌ ወጥቼ ግቢ ውስጥ በቀርቀሃ ከተሰራ አግዳሚ ወንበር ላይ አረፍ አልኩ። ከፊቴ ተንጧሎ በሚታየው ሰማይ ላይ አይኔን ተከያለሁ፤ ከዋክብቶች ዘርዘር ብለው ይታያሉ። ነፋሻማው ዓየር ዛፎቹን እያወዛወዘ የሚፈጥረው የሽውታ ድምጽ በሌላ በኩል ማርኮኛል።

ከከተማ ግርግር ከሰዎች ከበባ ወጣ ብሎ እንዲ ጸጥ ባለና ተፈጥሮ ብቻ ከሚያወራበት ቦታ መገኘት በእርግጥም ደስ ያሰኛል። ራስን ለማዳመጥ ከራስ ጋር ለመመካከር ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል።
🥰11👍6
March 27, 2024 1K