ሰላም የ ye-buna ቤተሰቦች! 👋 ለእናንተ የሚሆኑ ጥቂት አዳዲስ ማሻሻያዎችን እና ማሳሰቢያዎችን… — Ye-buna (የቡና) — TG.ME

ሰላም የ ye-buna ቤተሰቦች! 👋
ለእናንተ የሚሆኑ ጥቂት አዳዲስ ማሻሻያዎችን እና ማሳሰቢያዎችን ይዘንላችሁ መጥተናል፦

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) አማራጭ ተካቷል (0% ክፍያ): M-Pesa በገንዘብ ማውጣት (withdrawal) ላይ የ 1% ተጨማሪ ክፍያ መቁረጥ በመጀመሩ፣ ተጠቃሚዎቻችን ከተጨማሪ ወጪ እንዲድኑ የ CBE አማራጭን በ 0% ክፍያ አካተናል።

አሁን ያለምንም ተጨማሪ ቅናሽ በቀላሉ ገንዘብዎን በንግድ ባንክ ማውጣት ይችላሉ።

የ Meta Pixel ማስተካከያ ለ Facebook Ads ተጠቃሚዎች: በፌስቡክ ማስታወቂያ (Ads) የምታስተዋውቁ ክሬተሮች፣ የ Meta Pixel አሰራር በበለጠ ጥራት እና ቅልጥፍና እንዲሰራ ተደርጎ ተስተካክሏል። ዳሽቦርዳችሁ ላይ ገብታችሁ ሞክሩት!

ስለ ገንዘብ ማውጣት መዘግየት ይቅርታ እንጠይቃለን: ባለፉት ሁለት ቀናት በገንዘብ ማውጣት ማጽደቅ (withdrawal approval) ላይ ላጋጠመው መጠነኛ መዘግየት ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን። አሁን ላይ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተፈትቶ ስርዓቱ ወደ መደበኛ ስራው ተመልሷል 🙌
በቅርቡ ተጨማሪ አዳዲስ እና ድንቅ ፊቸሮች (features) ይዘንላችሁ እንመጣለን፤ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን! 🚀
❤22🔥6👍3
August 24, 2026 4K 11 5