ለye-buna.com ዲጂታል ፈጣሪዎች በሙሉ የተላለፈ ጠቃሚ ማሳሰቢያ ⚠️ የye-buna.com ማህበረሰብ… — Ye-buna (የቡና) — TG.ME

ለye-buna.com ዲጂታል ፈጣሪዎች በሙሉ የተላለፈ ጠቃሚ ማሳሰቢያ ⚠️
የye-buna.com ማህበረሰብ አባላት ጥራት ያለው እና ጠቃሚ ይዘት ለተጠቃሚዎች በማቅረብ እያደረጋችሁት ላለው ጥረት እናመሰግናለን። ሆኖም የማህበረሰባችንን ደህንነት ለመጠበቅ እና የህግ ተጠያቂነትን ለማስቀረት የሚከተለውን ጥብቅ መመሪያ እንድትተገብሩ እናሳስባለን።
በተለይ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሹ እና የህዝብን ደህንነት በቀጥታ የሚነኩ የዲጂታል ይዘቶችን (Ebooks፣ ቪዲዮዎች ወይም መመሪያዎች) በሙያው የተረጋገጠ እውቀት እና ፈቃድ ሳይኖራችሁ ማዘጋጀትና መሸጥ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ያለ በቂ የሙያ ማረጋገጫ መሸጥ የተከለከሉ ይዘቶች፦
የህክምና እና የጤና ምክሮች፦ መድኃኒት ማዘዝ፣ የህክምና ምርመራ ምክሮች፣ የክብደት መቀነሻ/መጨመሪያ ያልተፈተሹ አመጋገቦች ወይም የአእምሮ ጤና ማከሚያ መመሪያዎች።
የግብር እና የፋይናንስ ህጎች፦ ከህግ እና ከመንግስት የግብር ስርአት ጋር የተያያዙ ያልተረጋገጡ የኦዲት፣ የታክስ ማጭበርበር ወይም የፋይናንስ ምክሮች።
የፖለቲካ እና የመንግስት አስተዳደር ጉዳዮች፦ ህዝብን የሚያሳስቱ፣ የሀሰት መረጃዎችን የሚያሰራጩ ወይም የህግ ማዕቀፎችን የሚጥሱ የፖለቲካ ትንታኔዎች እና ፅሁፎች።
አደገኛ የኢንቨስትመንት ጥቆማዎች፦ ያልተረጋገጡ የGet-rich-quick (በአቋራጭ መበልፀግ)፣ ፒራሚድ ስኪሞች ወይም ህገወጥ የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎች።
አስቸኳይ እርምጃ እና የተጠያቂነት ማስተባበያ፦
• ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች የሙያ ብቃት ሳይኖራችሁ የለጠፋችሁት ማንኛውም ዲጂታል ምርት ካለ በአስቸኳይ ከመድረኩ እንድታነሱ (Remove እንድታደርጉ) እናሳስባለን።
• የመድረካችንን ፖሊሲ በመጣስ ለሚፈጠሩ ማናቸውም የህግ፣ የጤና ወይም የገንዘብ ጉዳቶች ye-buna.com ሙሉ በሙሉ ተጠያቂነት እንደማይወስድ እናሳውቃለን።
• መመሪያውን የማያከብሩ አካውንቶች ያለ ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ ከፕላትፎርሙ የሚታገዱ ይሆናል።
ትክክለኛውን እውቀት ለህብረተሰቡ በማድረስ ኃላፊነት የተሞላበት የፈጣሪነት ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
👍17❤10🔥2💯2🤝1
August 27, 2026 2.9K 52 5