ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንትነት ብመረጥ
1.አካዳሚክስ እና የትምህርት ጥራት (Academics & Quality) በተመለከተ
•የማጣቀሻ ቁሳቁስ (Handouts & Modules)፦ ለተማሪዎች የሚሰጡ የማስተማሪያ ግብዓቶች፣ ሃንድአውቶችና ሞጁሎች በተሟላ መልኩ እንዲደርሱ ክትትል ማድረግ
•ተማሪዎች በውጤት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ሲኖራቸው ያለ ምንም ፍርሃትና መሸማቀቅ ጥያቄዎቻቸውን በህግ አግባብ የሚያስረክቡበት እና ህብረቱ ተሟጋች የሚሆንበትን ግልጽ አሰራር መዘርጋት።
2.የተማሪዎች አገልግሎቶች በተመለከተ
•በግቢው ክሊኒክ ውስጥ ለተማሪዎች የሚሰጠውን የህክምና አቅርቦትና ፈጣን ምላሽ ማጠናከር።እንዲሁም በግቢው ውስጥ በዓመቱ የተከሰቱ 10 ከፍተኛ በሽታዎችን(top ten prevalence disease )በማጥናት የመድሃኒት ግዢ እነዚህን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ማድረግ ::
•ህብረቱ ማንኛውንም ትልቅ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት በተማሪዎች ማህበራዊ ገጾች ላይ የህዝብ አስተያየት መስጫ (Polls) በመክፈት የተማሪውን ቀጥተኛ ፍላጎት ማዳመጥ።
3.የመዝናኛ፣ የባህል እና የስፖርት ማዕከላት በተመለከተ
•የወንዶችና የሴቶች የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የቤት ውስጥ ጨዋታዎችን (Table Tennis, Chess) በየሴሚስተሩ በማዘጋጀት የተማሪዎችን የመዝናኛ አማራጭ ማሳደግ
•ዩኒቨርሲቲው ያለበትን የወልቂጤ ከተማና አካባቢውን ማህበረሰብ በበጎ አድራጎት ስራዎች (ለምሳሌ በነጻ የህክምና ምርመራ፣ የማስጠኛ ክፍሎች: የድጋፍ ትምህርቶች በመስጠት ...) ተማሪው የሚያገለግሉበትን ዕድል መፍጠር።
240
55
19
7
7
3
2June 15, 2026 16.5K 39 14