#NGAT
የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ብቻ የሚከናወን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡
የመመዝገቢያ ሊንክ 👇
https://ngat.ethernet.edu.et
ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ ያስፈልጋል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር ሲሆን፤ በምዝገባ ወቅት በቴሌብር በኩል መክፈል ይጠበቅባችኋል።
ምዝገባው በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚከናወን መሆኑን የገለፀው አገልግሎቱ፤ የፈተና ጣቢያዎች ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢ ቁጥሩ ታይቶ የሚወሰን መሆኑን ጠቁሟል፡፡
የፈተና መስጫ ጊዜው ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity

50
3July 25, 2026 13.7K 5 40