እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል‼ አዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 (ከአመዴ ገበያ ዝቅ ብሎ… — Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ — TG.ME

እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል

አዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 (ከአመዴ ገበያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ሸማ ተራ አካባቢ) በሱቆች ላይ ተከሰቶ የነበረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፈጣን የቁጥጥር ስራ በማድረጉ አደጋው ወደ ሌሎች የንግድ ተቋማት ሳይስፋፋ ማክሸፍ ተችሏል ብሏል።

ለአደጋው በቁጥጥር ስር መዋል የእሳት አደጋ ተከላካዮች ያደረጉት ሙያዊ ተጋድሎ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ትብብር እና የተቋማቱ የተቀናጀ ስራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተጠቅሷል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እና የደረሰው የጉዳት መጠን በባለሙያዎች እየተጣራ ይገኛል።
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤80😢19👏8😱5🕊3
September 5, 2026 12.1K 9