በጥይት ተማሪዋ የገደለው ተጠርጣሪ ከነመሳሪያው ተያዘ‼ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ ችራ… — Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ — TG.ME

በጥይት ተማሪዋ የገደለው ተጠርጣሪ ከነመሳሪያው ተያዘ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ ችራ ቀበሌ (አውሻሻ) ከጎንደር ወደ ወልቃይት/ዳንሻ ይጓዝ በነበረ አባዱላ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ እገታ እና ዝርፊያ ለመፈጸም ከጫካ ተኩስ የከፈተ ተጠርጣሪ ከነጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር ውሏል።

በተከፈተው ተኩስ በቅርቡ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቃ ወደ ቤተሰቦቿ በመመለስ ላይ የነበረች አንዲት ተማሪ ህይወቷ አልፏል።

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አበበ ወዝያለው እንደገለጹት፣ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የጸጥታ መዋቅሩ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ፈጣን ከበባና የተኩስ ልውውጥ ተጠርጣሪውን ከእነ ጦር መሳሪያው መያዝ ተችሏል።በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤106😭57👍36👏6🕊6🥰5😱5😢1👌1
September 5, 2026 25.1K 3