ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼
በደሴ ከተማ በተደጋጋሚ የመብራት ትራንስፎርመሮችንና የቴሌ መሠረተ ልማቶችን ሲዘርፉ የነበሩ ወንጀለኞች በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረትና ከግብረ-አበሮቻቸው ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
በጉዳዩ ላይ የኃላፊዎች አስተያየት፦
📌ኮማንደር ሠይድ አሊ (የደሴ ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ)፦ ዘራፊዎቹ መያዛቸው ትልቅ ስኬትና ህግን ማስከበር ማሳያ መሆኑን ገልጸው፣ ህዝቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ያለው ትብብር እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።
📌ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ (የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ)፦ ድርጊቱ ልማትን ለማደናቀፍ የተደረገ እኩይ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው፣ በልዩ ቡድን በተደረገ ምርመራ ውጤቱ እንደተገኘና ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራው እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
📌አቶ ሀብቱ አበበ (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደሴ ሪጅን ዳይሬክተር)፦ ከሐምሌ ወር ጀምሮ ይፈጸም የነበረውን ስርቆትና የንብረት ውድመት ለማስቆም ለተደረገው ከፍተኛ ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
📌ኮሎኔል ገዛህኝ አለባቸው (የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ሴኩሪቲ ማናጀር)፦ ተቋማቸው ጉዳዩን ከአጋር የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በትኩረት እየሰራበት እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
(መረጃው የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ህ/ግ ነው)
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
127
33
8
8
2
2
2
1
1September 5, 2026 22.8K 22









