አሰብን ለኢትዮጵያ ነፃ ወደብ አድርገናል" — የፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የ1991 ቃለ-መጠይቅ አነጋጋሪ… — Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ — TG.ME

"አሰብን ለኢትዮጵያ ነፃ ወደብ አድርገናል" — የፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የ1991 ቃለ-መጠይቅ አነጋጋሪ ሆኗል

የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኙ ማርቲን ፕላውት ይፋ ያደረገው እ.ኤ.አ. የ1991 የታሪክ ሰነድ አዲስ አነጋጋሪ ጉዳይ ይዞ ወጥቷል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በወቅቱ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃል መጠይቅ "አሰብን ለኢትዮጵያ ነፃ ወደብ አድርገን አውጀናል" ማለታቸውን ሰነዱ ያመላክታል።

የፖለቲካ ተንታኞች እይታ፦ኢትዮጵያ በአሰብ ወደብ ላይ ያላት ታሪካዊና ኢኮኖሚያዊ የመጠቀም መብት ገና ከጅማሪው በአስመራ እውቅና ተሰጥቶት የነበረ መሆኑን ያሳያል። • የባህር በር ጥያቄው በጦርነት የመወረር አላማ የሌለውና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ህጋዊ ጥያቄ መሆኑን ያረጋግጣል።

በወቅቱ የተደረገው ስምምነት በሽግግሩ ወቅት ለነበረው ሰላማዊ ግንኙነት ሲባል የተደረገ ጊዜያዊ ማዕቀፍ እንጂ ኤርትራ ሉአላዊ ሀገር ከሆነች በኋላ ግዛቷን አሳልፋ የምትሰጥበት የህግ ሰነድ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ።
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤94👍14🥰8😱6🕊5🙈1
September 4, 2026 14.9K 12