🚨 ያለፍላጎታቸው ሴቶችን በወሲብ ንግድ ላይ ያሰማሩ 5 ግለሰቦች በእስራትና በጥሬ ገንዘብ ተቀጡ‼
በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ አስተዳደር በመጠጥ ግሮሰሪ ንግድ ፈቃድ ሽፋን ሴቶችን ያለ ፍላጎታቸው ለወሲብ ንግድ ሲዳርጉና ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ አምስት ግለሰቦች እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ መቀጣታቸውን የከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
የሮቤ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ጌታቸው ታምሩ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት፤ ተከሳሾቹ በዘይበላ ወላሼ ቀበሌ «ኤል ክላሲኮ» በተባለ የምሽት ጭፈራ ቤት ሴቶችን በአስተናጋጅነት ካስቀጠሩ በኋላ በግዳጅ ለወሲብ ንግድ ያሰማሩ የነበረ ሲሆን፣ የሮቤ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።
⚖️ የተበየነው የቅጣት ውሳኔ፦
1ኛ ተከሳሽ ተሬሳ ፍቃዱ፦ ድርጊቱን በዋናነት በመምራትና በግዳጅ የመድፈር ጥቃት በመፈጸሙ 👉 በ23 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ200 ሺህ ብር መቀጮ
2ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ደሴ፦ 👉 በ10 ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር መቀጮ
3ኛ ተከሳሽ ወርቁ ደሜ፦ 👉 በ6 ዓመት እስራት እና በ45 ሺህ ብር መቀጮ
4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች (ተመስገን ፍቃዱ እና ቤክና መሐመድ)፦ 👉 እያንዳንዳቸው በ1 ዓመት ከ8 ወር እስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸዋል።(ብስራት ሬዲዬ)
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

137
35
18
5
4
4
4
3
3
2September 4, 2026 27.3K 10