በባህር ዳር ሰዎችን በማገት የተሳተፉ አምስት ተጠርጣሪዎች ተያዙ‼
በባህር ዳር ከተማ ሶስት ነጋዴዎችን አፍነው በመውሰድ ለ11 ቀናት አግተው ያቆዩ እና 3 ሚሊዮን 370 ሺህ ብር የተቀበሉ አምስት የወንጀል ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል ወንጀሉን የመራው በቀበሌ 06 የኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ባለቤት አብርሃም ጫኔ፣ ለእገታው የኮድ 04-04343 ቶዮታ ሂሉክስ የመንግስት ተሽከርካሪ ያዋለው አሽከርካሪ መለሰ፣ ታጋቾቹን በ170 ሺህ ብር ክፍያ ደብቆ ያቆየ የህንፃ አስተዳዳሪ እንዲሁም በገንዘብ ዝውውሩ የተሳተፉት አበበ ጌቴ እና ከአዲስ አበባ የተሳተፈ ተባባሪ ይገኙበታል።
ከነተሽከርካሪው በተጨማሪ አንድ ማካሮቭ እና አንድ ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውን የገለጸው ፖሊስ፤ የመንግስት ተቋማት በተሽከርካሪዎቻቸው ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ አሳስቦ ቀሪ ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ስራ መቀጠሉን አስታውቋል።(አማራ ፖሊስ)
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
83
21
8
8
4
3
2
1September 4, 2026 16K 27





