15 ዓመት እስራት ያስቀጣል‼ በአዲሱ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 550/2016 መሠረት፣ የትራፊክ ደንብ… — Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ — TG.ME

15 ዓመት እስራት ያስቀጣል

በአዲሱ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 550/2016 መሠረት፣ የትራፊክ ደንብ መጣስ የገንዘብ ቅጣት ብቻ ሳይሆን እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እና እስከ 15,000 ብር ቅጣት የሚያስከትል መሆኑ ተገለጸ።

በአዲሱ መመሪያ መሠረት፡
📌ከፖሊስ ጋር አለመተባበር፡ አሽከርካሪዎች መረጃ ለመስጠት አለመተባበር ወይም የትራፊክ ፖሊስን ማደናቀፍ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል።

📌በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፡ በቸልተኝነት የሰው ሕይወት ወይም አካል ላይ አደጋ ማድረስ እስከ 15 ዓመት እስራት እና እስከ 15,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ያስከትላል።

📌የመንጃ ፈቃድ እገዳ፡ ከእስራትና ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ የቅጣት ነጥብ በመመዝገብ የመንጃ ፈቃድ እገዳ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።

ኤጀንሲው ሕጉ መክበዱን ገልጾ፣ አሽከርካሪዎች ሕጉንና ሕሊናቸውን መሠረት አድርገው እንዲያሽከረክሩ ጥሪ አስተላልፏል።
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤139😱20👏16🕊15😢5💩4🙈4🔥2❤‍🔥1
September 2, 2026 29.5K 72