ለጤና ባለሙያዎች የተሰጠ ምላሽ‼ የአማራ ክልል የጤና ዘርፍ የትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያ መመሪያ (ቁጥር… — Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ — TG.ME

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድዱቲ መመሪያ ቁጥር 682018 (2) (1) (1).pdf
ለጤና ባለሙያዎች የተሰጠ ምላሽ

የአማራ ክልል የጤና ዘርፍ የትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያ መመሪያ (ቁጥር 68/2018) ማጠቃለያ

​የ24/7 የህክምና አገልግሎትን ሳያቋርጡ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የወጣው አዲሱ መመሪያ ዋና ዋና ነጥቦች፦

💰 1. የትርፍ ሰዓት አከፋፈል ስሌት (ከሥራ ግብር ነፃ)፦
የሥራ ቀናት (ምሽት 12፡00 - 4፡00)፦ የመደበኛ ሰዓት × 1.25
የሥራ ቀናት (ምሽት 4፡00 - ንጋት 12፡00)፦ የመደበኛ ሰዓት × 1.5
ቅዳሜና እሁድ (የእረፍት ቀናት)፦ የመደበኛ ሰዓት × 2.0
የሕዝብ በዓላት ቀናት፦ የመደበኛ ሰዓት × 2.5
ተጠባባቂ (On-call)፦ ካልተጠሩ 30% | ተጠርተው ከሰሩ 100%

⚠️ 2. ዋና ዋና የአሰራርና የዲሲፕሊን ሕጎች፦
• በወር ከ212 ሰዓት በላይ መስራት አይቻልም (ልዩ ሁኔታዎች ካልተፈቀዱ በስተቀር)።
• የትርፍ ሰዓት ሰርቻለሁ በሚል ከመደበኛ ሥራ መቅረት ወይም መዘግየት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
• በሥራ ክፍል አልጋ ማስገባትና በስራ ሰዓት ወጥቶ መጥፋት ተጠያቂነት ያስከትላል።

📅 3. የተገቢነት ጊዜ፦
መመሪያው ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ሲሆን፣ በስታንዳርዱ መሰረት የተሰራው የስምሪት አሰራር ደግሞ ከመስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል።
መመሪያው ከላይ ተያይዟል።
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤87🙏7🕊6🙈4🤝4🏆3🥰2💯2🍾2🌭1
September 3, 2026 22.9K 87