update‼
"ዩኒቨርሲቲው ሙሉ በሙሉ ተቃጠለ የሚባለው ሀሰት ነው"የዩኒቨርሲቲው አመራሮች
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ህንፃ ላይ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት ገደማ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዩኒቨርሲቲው አመራሮች አስታወቁ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር) እና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እንደገለጹት፤ አደጋው የተከሰተው በኤሌክትሪክ ኮንታክት ምክንያት በህንፃው ሶስተኛ ፎቅ ላይ ሲሆን፣ እሳቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በአደጋው የህንፃው ጣሪያ እና መስኮቶች ላይ ጉዳት ቢደርስም፣ ከውስጥ የነበሩ ንብረቶች ቀድመው በመውጣታቸው በንብረት ላይ የጎላ ጉዳት አልደረሰም።
አመራሮቹ አደጋው የደረሰው ቢሮዎች እና ላብራቶሪዎች ባሉበት ህንፃ ላይ እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ እንደሚወራው "ቤተ-መፅሐፍት" ላይ አለመሆኑን እና ዩኒቨርሲቲው ሙሉ በሙሉ ተቃጠለ የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

100
7
7
4
3
2
2September 3, 2026 30.1K 7