ለፖሊስ ፈረስ የገዙት የቀበሌው ነዋሪዎች ተግባር እያነጋገረ ነው‼ "ፖሊሶች በእግራቸው መንከራተታቸው… — Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ — TG.ME

ለፖሊስ ፈረስ የገዙት የቀበሌው ነዋሪዎች ተግባር እያነጋገረ ነው

"ፖሊሶች በእግራቸው መንከራተታቸው አሳዝኖናል፤ ስንጠራቸውም በፍጥነት እንዲደርሱልን ይረዳቸዋል" በማለት ለፖሊሶች የፈረስ መጓጓዣ ገዝተው ያበረከቱት የቀበሌው ነዋሪዎች መነጋገሪያ ሆነዋል።

​በካፋ ዞን ሸሾ እንደ ወረዳ ከሚገኙ 32 ቀበሌዎች መካከል የማራሃሻኪያ ቀበሌ እና የኦሮራ ቀበሌ ህበረተሰብ ክፍሎች ፖሊስ በአካባቢያቸው በፍጥነት ደርሶ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሁለት የግልቢያ ፈረሶችን በመግዛት ለአገልግሎት እንዲውሉ አድርገዋል።

​የወረዳው ፖሊሶችም ለተሰጣቸው ፈረሶች አመስግነው፣ ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል እና የአካባቢውን ሰላም ለማስከበር የህዝብ ተሳትፎ ምን ያህል ወሳኝ መሆኑን ያሳየ ትልቅ ተግባር ነው ብለዋል። Via Behaja News
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤170👏43👌12🙏10🥰8😱6🙈5🏆4🕊3😍3
September 2, 2026 30.3K 7