የቻይናው ፕሬዝዳንት ግብፅ ገብተዋል‼
📌የቻይና-ግብፅ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና የዓባይ ወንዝ የወደፊት አቅጣጫ‼
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ከ10 ዓመታት በኋላ በግብፅ ባደረጉት ጉብኝት ከፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ ጋር ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸው ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ወቅት ግብፅ «ታይዋን የቻይና አካል ናት» የሚለውን አቋም የደገፈች ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትም በከፍተኛ ደረጃ መጠናከሩ ተገልዟል።
በሌላ በኩል፣ ይህ የቻይና እና የግብፅ መቀራረብ ከኢትዮጵያ እና ከዓባይ ወንዝ (ታላቁ ህዳሴ ግድብ) ጋር ባለው የጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ ያላቸዉ ሚና ትኩረት ስቧል::
📌ቻይና ከኢትዮጵያ ጋርም ጠንካራ የኢኮኖሚ እና የታላቅ ወዳጅነት ግንኙነት ያላት በመሆኑ፣ በሁለቱ ሀገራት (በኢትዮጵያ እና በግብፅ) መካከል ባሉ አለመግባባቶች ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ ከመግባት ይልቅ በጥንቃቄ የተሞላ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንደምትከተል ይጠበቃል።
📌 የዓባይ ወንዝ መነሻዋ ኢትዮጵያ ሆና እያለ ግብፅ የወንዙን ውሃ «የእኔ ብቻ ነው» ማለቷ ዘላቂ መፍትሔ እንደማያመጣ የተጠቆመ ሲሆን፤ ብቸኛው አማራጭ በጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) መርህ ላይ ተመስርቶ አብሮ መስራት ብቻ እንደሆነ ተገልዟል።
📌 ግብፅ ቀደም ሲል የነበራትን ግትር አቋም በመቀየር በዲፕሎማሲና ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑ ተጠቅሷል።
📌የዓባይ ወንዝን በተመለከተ ዘላቂ ሰላምና ልማት ሊመጣ የሚችለው ሀገራት ሀብቱን በጋራ እና በፍትሃዊነት ሲጠቀሙበት ብቻ እንደሆነ ተመልክቷል።
#WasuMohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

96
13
6
6
4
3September 4, 2026 26.9K 4