በመጨረሻም ሰላማዊ ሰልፉ ተከለከለ‼ 📌ደሴ ገራዶ ከ10 በላይ ወጣቶች ሰልፍ አስተባበራችሁ በሚል በሚኒሻ… — Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ — TG.ME

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድPhoto
በመጨረሻም ሰላማዊ ሰልፉ ተከለከለ

📌ደሴ ገራዶ ከ10 በላይ ወጣቶች ሰልፍ አስተባበራችሁ በሚል በሚኒሻ ታፍነው የት እንደተወሰዱ አይታወቅም ተብሏል

📌ገራዶ ነዋሪዎችን በየሰፈሩ በሚኒሻ ማዋከቡ ማሸማቀቁ ብዙዎችን አሳዝኗል ነው የተባለው

ደሴ ከተማ በተለይ የሰኞ ገበያ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲና የፀጥታ አመራሮች ገራዶ ምን እያካሄዳችሁ ነው?

የምትመሩት ህዝብ የገራዶ መነሃሪያ በክልልና በከተማው ከፍተኛ አመራሮች ከተመረቀ በኋላ ተክደናል:ስራ ሊጀምርልን ስላልቻለና ሰሚ አካል ስላጣን ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን ብለው በህጋዊ መልኩ ተነሱ።

የእናንተ በዚህ ደረጃ በሰልፍ ጥያቄያቸውን እንዳያቀርቡ ማዋከቡ ምን ይሉታል? ይታወቃል የፖለቲካ ጉዳይ የላቸው።

ከነዋሪዎች በተገኘ መረጃ መሠረት እስካሁን ደሴ ገራዶ ከ10 በላይ ወጣቶች ሰልፍ አስተባበራችሁ በሚል በሚኒሻ ታፍነው የት እንደተወሰዱ አይታወቅም ተብሏል።ያሳዝናል።

የክፍለ ከተማችሁ ህዝብ በዛ ልክ ለልማቱ ሲቆረቆር እናንተ መርቀው ዞር ያሉ ኃላፊዎቻችሁን ከመጠየቅና ምክንያታዊ መልስ እንድሰጥ ከማድረግ ይልቅ በኮሚቴውና ወጣቱ ላይ በዛ ደረጃ ዛቻና ማሸማቀቅ በእውነት አሳፋሪ ነው።

ህዝቡ ልማቱን ጠየቀ እንጅ ለፖለቲካ ጉዳይ ሰልፍ ልውጣ አላለም።ደብዳቤው ተያይዟል።"ብልፅግና ወስኖላችኋል" ተብለው የተካዱት እነሱ ቢያንስ ኃላፊነታችሁን ተጠቅማችሁ ክቡር ከንቲባው ለህዝቡ መልስ እንድሰጡ ማድረግ ሲገባችሁ በየቤቱ አፈናና ማሸማቀቅ ያሳዝናል።

ነዋሪዎች ጥያቄያቸው የልማት እንጂ የፖለቲካ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ገልጸዋል፣ የመንግሥት አካላት አፈሳና ማሸማቀቁን አቆመው ለመናኸሪያው ሥራ መጀመር አወንታዊ ምላሽ እንዲሰጡም ጠይቀዋል።

ወጣቶቹ በአስቸኳይ ቢለቀቁ መልካም ነው።ፖሊስ ጣቢያ ታይቷል የሉም ነው የተባለው።ከወሰዳችሁበት መልሷቸው።ትክክል ያልሆነ ስራ እየሰራችሁስለሆነ ራሳችሁን መልከቱ።
📌መነሃሪያውን በተመለከተ እነዚህን ቀደምት ዘገባዎች ገብታችሁ እዪቸው👇
፩ .https://www.facebook.com/61569879454961/posts/122147406512662648/?app=fbl
፪. https://www.facebook.com/share/v/1K5dWLCtJJ/
፫. https://www.facebook.com/share/p/1c5guNKrHK/
፬. https://www.facebook.com/share/p/1BeHqPiDkd/

https://www.facebook.com/share/r/19QSn6mRHR/
❤117💔50😭14🤝11👌7🙈5💯4🍾3🥰2🏆2
September 2, 2026 27.6K 5