"ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ዛሬ አሳውቀናል"የደሴ ገራዶ አካባቢ ነዋሪዎች
ከአራት ወራት በፊት ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የደሴ ከተማ አመራሮች ተገኝተው በይፋ የተመረቀው የደሴ ገራዶ መናኸሪያ ወደ ስራ ባለመግባቱ ነውዋሪዎች ተደጋጋሚ ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ገራዶ መነሃሪያ ስራ እንድጀምር "ብልፅግና"ወስኖላችኋል ብለው በምርጫ ዋዜማ ለህዝቡ መናገራቸውን ተከትሎ ህዝቡ ድምፅ ከሰጠን በኋላ "ተካድን" ሲል እንደነበር በቀደምት ዘገባዎች መገለፅ ይታወሳል።
በመጨረሻም ለነሐሴ 28/2018ዓም ህዝቡ ለሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የእወቁልን ደብዳቤ ዛሬ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማስገባታቸውን ከኮሚቴዎቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ክቡር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እርሶና ካቢኔዎ ለደሴ ከተማ ልማት ያደረጋችሁት ትጋት ያመጣችሁት ለውጥ በቀላል የሚታይ አይደለም።ምስጋና ይገባችኋል።አሁን ባለቀ መነሃሪያ ከህዝብ ጋር እልህ ውስጥ የሚያጋባችሁ ነገር በመፍጠር ስራችሁን ስታጠለሹ መታየት የለበትም።
ምናልባት ነዋሪዎቹ በተደጋጋሚ እንደሚያነሱት የተለየ ትስስር እስከሌለ ድረስ እርስዎ በአንደበትዎ ተናግረው ህዝብ በቃልዎ ተደስቶ መርቆ አሜን ብለው እንደት ተመልሶ እንደዚህ ይደረጋል? የክልሉን ም/ፕሬዝደንት ይዘው ሪቫን ቆርጠው መርቀው ነገሩኮ አያምርም።እባኮ ክቡር ከንቲባ መፍትሄ ስጡበት‼
ንግግርዎ👇እዚህ አለ
https://t.me/wasulife/52228
📌መነሃሪያውን በተመለከተ እነዚህን ቀደምት ዘገባዎች ገብታችሁ እዪቸው👇
፩ .https://www.facebook.com/61569879454961/posts/122147406512662648/?app=fbl
፪. https://www.facebook.com/share/v/1K5dWLCtJJ/
፫. https://www.facebook.com/share/p/1c5guNKrHK/
፬. https://www.facebook.com/share/p/1BeHqPiDkd/
፭
https://www.facebook.com/share/r/19QSn6mRHR/
106
18
5
2
2
1
1
1August 26, 2026 30.7K 6



