"ከተማ አስተዳደሩ የገራዶ መነሃሪያ ስራ መጀመር ጥቅማቸውንን ይነካል በሚሉ አካላት ተጠልፏል" የደሴ ገራዶ አካባቢ ነዋሪዎች
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የደሴ ከተማ አመራሮች ተገኝተው በይፋ የተመረቀው የደሴ ገራዶ መናኸሪያ፣ ከተመረቀ ወራት ቢቆጠሩም እስከ ዛሬ አገልግሎት አለመስጠቱ የአካባቢውን ነዋሪዎች ከፍተኛ ቅሬታና ምሬት ውስጥ ከቷል።
"ከተማ አስተዳደሩ የገራዶ መነሃሪያ ስራ መጀመር ጥቅማቸውንን ይነካል በሚሉ አካላት ተጠልፏል" የሚሉት ነዋሪዎቹ መነሃሪያው ከተገነባ ወደ ስድስት ዓመታት ገደማ ቢሆነውም ወደ ሥራ ባለመግባቱ ማኅበረሰቡ ለከፍተኛ ችግር እንዳጋለጣቸው ገልጸዋል።በተለይም መሬታቸውን ለልማት የለቀቁ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው በመናኸሪያው ሥራ ያገኛሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎ የነበረ ቢሆንም፣ መናኸሪያው በመዘጋቱ ምክንያት ወጣቶቹ ያለሥራ ለአልባሌ ቦታዎችና ለሱሶች እየተዳረጉ ይገኛሉ። ነዋሪዎቹ ሁኔታውን ሲገልጹ "ከተመረቀ በኋላ ተክደናል" ብለዋል። በመነሃሪያው ተስፋ ምክንያት ሃብታቸውን ያፈሰሱ አልሚዎችም ቅሬታቸው ተመሳሳይ ነው።
በቪዲዬ እንደተገለፀው የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ለሕዝቡ ባደረጉት ንግግር፦
"..መነሃሪያው ስራ እንድጀምር ..የከተማ አስተዳደሩ እና ፓርቲው ወስኖላችኋል፤ እንግዲህ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ነው!" ብለው ህዝቡን አስደስተው በአባቶችና እናቶች ተመርቀው ነበር።
ከንቲባው ህዝብ ሰብስበው በይፋ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ በተግባር ግን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አለመኖሩን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
ቀደም ሲል መናኸሪያው አገልግሎት እንዳይጀምር "መከላከያ አለበት" የሚል ምክንያት ይቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ ኮሚቴውና ነዋሪዎቹ ከሠራዊቱ አመራሮች ጋር በመነጋገር መከላከያ ቦታውን ለቅቆ እንዲወጣ መደረጉ ተገልጿል። ሆኖም መከላከያ ቦታውን አክብሮ ከለቀቀ በኋላም የከተማው አስተዳደር መናኸሪያውን ለማስጀመር ፍላጎት በማጣቱ ሰበብ ማጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
አሁን ላይ የመጨረሻ ምሬት ላይ መድረሳቸውንና አስተዳደሩ በአስቸኳይ ችግሩን ፈትቶ መናኸሪያውን ወደ ሥራ እንዲያስገባላቸው ጠይቀዋል።ምላሽ ካላገኘ ግን ቅሬታቸውን እስከ መጨረሻው የመንግስት ርከን ለማቅረብና ሰላማዊ ሰልፍ ጭምር ለማድረግ እንደሚገደዱ ይታወቅልን ብለዋል።በጉዳዩ ላይ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
ቪዲዬ:-ከንቲባው አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ገራዶ ተገኝተው የተናገሩት ነው።
📌መነሃሪያውን በተመለከተ እነዚህን ቀደምት ዘገባዎች ገብታችሁ እዪቸው👇
፩ .https://www.facebook.com/61569879454961/posts/122147406512662648/?app=fbl
፪. https://www.facebook.com/share/v/1K5dWLCtJJ/
፫. https://www.facebook.com/share/p/1c5guNKrHK/
፬. https://www.facebook.com/share/p/1BeHqPiDkd/
#WasuMohammed
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
120
25
4
3
3
3August 19, 2026 33.9K 9