23/12/2018 ማቴዎስ 21:18-23 በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ… — ፀዊረ መስቀል — TG.ME

23/12/2018
       ማቴዎስ 21:18-23


     በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች። ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች? ብለው ተደነቁ። ኢየሱስም መልሶ አላቸው እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር፡ ብትሉት ይሆናል፤ አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ........

1 ቆሮንጦስ 13:1-ፍጻሜ
1 ጴጥሮስ 5:6-12
ሐዋ.ሥራ 12:18-ፍጻሜ


👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ፤ አው ዘወልደ ነጐድጓድ
                                      
ምስባክ
         መዝሙር 45:2-3


ወለእመኒ ፈለሱ አድባር ውስተ ልበ ባሕር

ደምፁ ወተሐምጉ ማያቲሆሙ

ወአድለቅለቁ አድባር እምኃይሉ

ትርጉም


ስለዚህ ተራራዎችም ወደባሕር ልብ ቢወሰዱ

ውሃዎቻቸው ጮኹ ተናወጡም

ተራራዎችም ከኀይሉ የተነሣ ተናወጡ
❤1
August 28, 2026 150 1