19/12/2018 ማቴዎስ 27:50-57 ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ያንጊዜም ነፍሱ፤ ከሥጋው… — ፀዊረ መስቀል — TG.ME

19/12/2018
         ማቴዎስ 27:50-57


      ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ያንጊዜም ነፍሱ፤ ከሥጋው ተለየች። እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተነዋወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ። መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተው ከነበሩ ከቅዱሳን በድኖችም ብዙዎች ተነሡ። "ከመቃብራቸውም ወጡ፤ ከትንሣኤውም በኋላ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩአቸው። "የመቶ አለቃውና ከእርሱ ጋር ጌታችን ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት ግን፤ ንውጽውጽታውንና የሆነውን ሁሉ አይተው እጅግ ፈሩ፤ “በእውነትም ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው” አሉ። የሆነውንም ሁሉ ከሩቁ የሚመለከቱ ብዙ ሴቶች በዚያ ነበሩ፤ እነርሱም ከገሊላ ጀምሮ ጌታችን ኢየሱስን የተከተሉትና ያገለገሉት ነበሩ። "ከእነርሱም ማርያም መግደላዊት፥ የያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም፥ የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ነበሩ....

ሮሜ 1:8-15
1ጴጥሮስ 3:8-15
ሐዋ፡ሥራ 16:35-ፍጻሜ


👉 ቅዳሴ ዘእግዝእትነ አው ግሩም

ምስባክ
        መዝሙር ፶፭ : ፲ - ፲፩


በእግዚአብሔር እሴብሕ ቃልየ

በእግዚአብሔር ይከብር ዘነበብኩ

ወበእግዚአብሔር ተወከልኩ ኢይፈርህ ምንተ ይሬስየኒ ሰብእ

ትርጉም


በእግዚአብሔር ቃሌን አከብራለሁ

የተናገርሁትም በእግዚአብሔር ዘንድ ይከብራል

በእግዚአብሔር ታመንሁ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል
❤1
August 24, 2026 342 1