ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ። እንኳን ለሰ/ት/ቤታችን 58ኛ ዓመት የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። የሰ/ት/ቤታችንን ዓመታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ አቡቀለምሲስ ቤተ-መጽሐፍ የመጽሐፍ ማሰባሠብ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም ለእናት ፍቁረ እግዚእ የልደት በዓል የሚሆን ስጦታ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብጹዕ ነዉ በሚለዉ አምላካዊ ቃል መሠረት ሁላችንም በምንችለዉ አቅም አንዳንድ መንፈሳዊ መጽሐፍ በማበርከት የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአምላከ ቅዱስ ዮሐንስ ስም እናሳስባለን።
ትምህርት ክፍሉ!!!










