ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለወልይነትና ቅደስና ቀርቶ እንደው በእውነቱ በጣም ስኬታማ መሪ ነው ብለንስ ልንጠቅሰው የምኝችል መሪ ነው ወይ?
ያለፉት ስምንት አመታት የአመራር ዘመን ውጤቱን ስናይ የሚያሳየን እርሱን ነው ወይ?
እርግጥ ነው አብይ አህመድ በተለያዩ ዘርፎች የተለያዩ ስኬቶችን መጎናፀፍ ችሏል። በተለይም በከተማ ልማት ፤ የታጣቂዎችን ግስጋሴ በመግታት ፤ ሀገሪቱን ከመበታተን በማዳን እና ግዙፍ መከላአያ ሰራዊት ስኬታማ አይደለም ብሎ ማስተባበል አይቻልም።
ግና የአብይ አህመድ መንግስት የወደቀባቸው በርካታ ውድቀቶችን ዩያዘ መንግስት ነው።
👉 ሰላም እጅግ በመደፍረሱ ዜጎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ያልቻሉበት
👉 የእርስበርስ ጦርነት የሀገሪቱ ዋነኛ መገለጫ የሆነበት
👉 የዋጋ ንረቱና የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ እጅግ መዳከም አይደለም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የመኖር ህልውና እንኳ የተፈታተነበት ድሀውን ህዝብ ተስፋ ያስቆረጠበት
👉 ሀገሪቱ በእዳ ተውጣ የኢኮኖሚ ሉአላዊነቷን አጥታ እጅና እግሯን ለ IMF ያስረከበችበት
👉 የትምህርት ስርአቱ ሙቶ ከ 10% በታች ተማሪዎች ብቻ እያለፉ እነርሱም ስራ የማያገኙበት!
👉 የዩኒቨርስቲ ትምህርቶች መክፈል ለሚችሉ ብቻ እንዲሆን እየተደረገ የመደብ ልዩነት ከ ግማሽ ምእተአመት በሗላ እንደገና የተፈጠረበት
👉 ሙስናና ብልሹ አሰራር ሀላል የወጣበት
👉 የስራ አጥነቱ ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከሀገር ለመውጣት ህይወታቸውን ቀብድ አሲዘው እየተሰደዱ ያሉበት!
👉 ማህበራዊ ቀውስ የገነነበት ፤ የሀይማኖቶና የብሔር ሽኩቻ ጥላቻና መከፋፈል አየሩን የሞላበት!
👉 በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችች በረሀብ እየተሰቃዩ በትሪሊዮን የሚቆጨር ገንዘብ ውበትና ቤተመንግሥት ግንባታ ላይ የሚረጭበት
👉 የሀገሪቱ አለምአቀፍ ቅቡልነትና ተፅእኖ ፈጣሪነት የቀነሰበት
👉 ልክ ያጣ ግብርና በሌብነት የታሸ የግብር አሰባሰብ ብዙዎችን አስመርሮ ከገበያ ውጭ ያደረገበት!
ኧረ ስንቱ ነው ተዘርዝሮ የሚያልቀው!
እና ከስኬታማነት መሪነትም አሳልፈው ለማንቆለጳጰስ ቃል የሚያጥራቸው ሰዎች ግን እነርሱ የሚያዩበትን መነፅር ለእኛም ቢያውሱን!
በመሰረቱ ለእኔ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለውን የህዝብ ድጋፍ አግኝቶ በሚገባ ያልተጠቀመ መሪ ነው። ያን እድል ወደ ስትራቴጂካዊ ውጤት ቢቀይረው ኖሮ ዛሬ በዚህ የስቃይ ደረጃ አንሆንም ነበር።
ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
Telegram
Seid Social
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

85
23
13
3
3
1August 30, 2026 6K 27 8