ሌላው ጫት የሚያመጣው ጥፋት በሚቅምበት ወቅት አንድ ሰው ለራሱ ፈፅሞ የተጋነነ እና የሌለ ማንነት እንዳለው… — Seid Social — TG.ME

ሌላው ጫት የሚያመጣው ጥፋት በሚቅምበት ወቅት አንድ ሰው ለራሱ ፈፅሞ የተጋነነ እና የሌለ ማንነት እንዳለው እንዲያስብ ማድረጉ ነው። ይህ ከስካር የሚመጣ ሽወዳ ነው። ምርቃና ልትሉት ትችላላችሁ።
እና ያሰው በዚያ ቅፅበት ብዙ ድንበሮችን ያልፋል።
ራሱን ባለከራማ እና ወልይ አድርጎ ይቆጥራል።

እርሱ በእፁ ውስጥ የሚያቸው ምስሎች እርሱ ልዩ ስለሆነ የሚታዩት ይመስለዋል። የርሱ ዱአ ከሌላው ዱአ ሁሉ የተለየ ኢባዳው ከሌሎች ሁሉ የበለጠ መስለው ይታዩታል። እናም በሁሉም ነገሮ ድንበር ያልፋል።

ተናንሳችሁ እና ፈርታችሁ ለምኑኝ ያለውን አላህን እርሱ ይዳፈረዋል። ትእዛዝ በሚመስል አነጋገር ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አድርግ ይለዋል።
ኧረ ከዚያም አልፎ ለራሱ አድርጌዋለሁ ይለዋል።
ይህን ጀባ ብየሀለሁ ፤ ይሄን ሰጥቼሀለሁ ይሄን አድርጌልሀለሁ እያለ እየቆጠረ ማስረከብ ሁሉ ይጀምራል።

እንዲህ አይነት መሸወዶች ዱአ እና ኢባዳ ላይ ብቻ ሳይሆን በመደበኛ ህይወትም ላይ ያጋጥማሉ። የሚቅም ሰው በሚቅምበት ወቅት ሌላ አለም ላይ ያለ ነው የሚመስለው። ከዚያ ምርቃና ወይንም ስካር ሲወጣ ያያቸው ነገሮች ሁሉ እንደ ጉም ሲተኑበት ያያል። ድባቴ ውስጥ ይገባል ። እንደገና ያንን የሚያምር ምስል ለመከሰት መልሶ መቃም አለበት።

እኔም ጫት አውዳሚ ነው። ከመስጅድ አይደለም ከመስጅድ አካባቢ እንኳ መኖር የሌለበት እፅ ነው።
በነገራችን ላይ ባንኮች በኢስላማዊ ፋይናንስ ዘርፍ ለጫት አያበድሩም ከጫት የሚገኝንም ገቢ ወደ ወለድ ነፃ አካውንት ገቢ እንዲደረግ አይፈቅዱም።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
❤83👍32😁6🥰2🤯1💯1
August 27, 2026 7.4K 35 17