ከእስልምና ጋር ምንም ግንኙነት ከሌላቸውና በብዙ ሙስሊሞች ከሚዘወተሩ ነገሮች አንዱ ጫት ነው።
በርግጥ አሁን እንኳ ሁሉም ሀይማኖት ሳይለይ እያነጀበበት ያለ ነገር ሆኗል።
እኔ በተለይ መስጅድ ውስጥ ጫት ሳይ በጣም ነው የሚያበሳጨኝ።
ጫት ሀራም ነው ሀላል ነው ፤ ኸምር ነው አይደለም የሚለውን ብንተወው እንኳ የጫት መቃም ውጤት አስቀያሚ መሆኑን ማስተባበል የሚቻል አይመስለኝም።
ጫት ከኢስላም ጋር ፣ ጫት ከዱአ ጋር ፣ ጫት ከአዝካር ጋር የሚያገናኛቸው አንዳችም ነገር እንደሌለ በፅኑ አምናለሁ።
ዱአ ተዋዱእን ይፈልጋል ፤ አዝካር አደብን ይጠይቃል ፤ በኹሹእና ሰኪና የሆነ ጊዜ ሁሉም ጣእሙን ያገኛል።
በተለይ ለወጣቶች ጫት በደረሰበት ባይደርሱ ወንድማዊ ምክሬ ነው። ብዙ ነገሮችን ቀስበቀስ እያሳሳበ የሚያወድም እንደ ጫት አላየሁም።
ብዙ ትዳሮች ተናግተዋል ፤ የብዙዎች ኢኮኖሚ ተቃውሷል ፤ ብዙ ውበቶች ረግፈዋል ፤ ብዙ ወጣትነትም ጠንዝሏል።
እርግጥ ነው በሀገራችን ብዙ ዛውያዎች ላይ ለመነቃቃት እያሉ ጫት የሚቅሙ አሉ። ያ ነገር እንደ ኢባዳ አካል ተደርጎ እንዲወሰድ ብዙዎችን ያሳተ ይመስለኛል።
ጫት በአብዛኛው የሚበቅለው ሙስሊሙ ባለበት ሞቃታማው ክፍል በመሆኑ ደግሞ የበለጠ ተጋላጭ ያደረገን ይመስለኛል።
የሆነው ሆኖ አንድ ሰው በህይወቱ ጥሩ ለመሆን ከየትኛውም ሱስ ነገሮች ሁሉ ራሱን ቢቆጥብ በእጅጉ ይመከራል።
ጫት ሰአትንም ኢነርጅንም ህልምንም የሚሰርቅ ነገር ነው።
ቢያንስ ቢያንስ ደግሞ ሰው አላማውን ሳያሳካ እንዲህ ወዳለ አውዳሚ ሱስ ባይገባ ወንድማዊ ምክሬ ነው።
ጫት ብቻውን የሚቆም ሱስም አይደለም። ሌሎች ሱሶችን እየጎተተ የሚያመጣ የሱስ ማግኔት ነው።
ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
119
31
24
4
1August 26, 2026 8.1K 40 22

