የሳኡዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሸይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊ በሞት እንዲቀጡ ጠይቋል።
ሸይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊ በአሁኑ ሰአት በሳኡዲ እስርቤት ውስጥ ሆነው ጤናቸው ክፉኛ መቃወሱን የሳኡዲ እስረኞችኝ የሚከታተለው የህሊና እስረኞች አስታውቋል።
ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ አቃቤህጉ ሸይኹ እንዲገደሉ ፍርድቤቱን ጠይቋል።
ሽይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊ በዘመናችን ከሚገኙ ታላላቅ አሊሞች አንዱ ሲሆኑ በጥልቅ የፊቅህና የሀዲስ ዘርፍ በጣም ሊቅ ናቸው።
ሸይኹ ሳኡዲ አረቢያ እየሄደችባቸው ያሉትን ከኢስላም የሚጣረሱ አካሔዶች የሚተችና አልአረቢያ ቴሌቪዥን እያሰራጨ የሚገኘውን ከኢስላም ያፈነገጡ ፊልሞችና አስተምህሮቶችን የሚተቹ ፅሁፎችን ካስነበቡ በሗላ ከ 10 አመት በፊት ወህኒ ቤት ተወርውረዋል። እዚያም ምንም ክስ ሳይመሰረትባቸው የ 10 አመታት ስቃይ ቢያሳልፉም አሁን ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሞት እንዲቀጡ ፍርድቤትን መጠየቁ ብዙዎችን አስደንግጧል።
ከሸይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊ በተጨማሪ ሸይኽ ሰልማኑል አውዳ ፤ ሸይኽ ኻሊድ አልራሽድ ፤ ሸይኽ አዋድ አልቀርኒ ፤ የመስጅደል ሀረም ኢማም ሸይኽ ዶክተር ሳልህ አልጧሊብ ፤ ሸይኽ ሰፈር አልሀዋሊ ይገኙበታል።
በእስር ላይ እያሉ ተሰቃይተው በቶርቸርና በረሀብ የሞቱ በርካታ ኡለማኦች ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል
ሸይኽ ፈህድ አልቃዲ ለሳኡዲው ንጉስ የምክር ደብዳቤ በመፃፋቸው ታስረው የነበሩ
ሸይኽ አህመድ አልአማሪ
ፕሮፌሰር ሸይኽ ሙሳ አልቀርኒ
ዶክተር አብዱሏህ አልሀሚድ ወዘተ ይገኙበታል።
ሸይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊን ጨምሮ ሸይኽ ሰልማኑል አውዳ ፣ ሸይኽ አዋድ አልቀርኒ እና ሸይኽ አሊ አልኡማሪ የሞት ቅጣት የሚጠብቃቸው ኡለሞች ናቸው።
ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
114
39
27
6
3
2
1August 26, 2026 7.4K 47 24

