ስለ ውዱ ነብይ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የሚፅፉና የሚናገሩ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖቻችን ገፅ ስር ገብቶ
" መውሊድ ቢዲአ ነው ፤ መውሊድ ሽርክ ነው" እያለ እንደሚፅፍ ሰው ግን አህመቅ አለ በአሏህ?
ምን አይነት የአስተሳሰብ መካንነት ነው?!
ሰው እንደት ቦታና ጊዜ እንኳ አይመርጥም!
እነዚያ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች የበለጠ በሚወሱበት ወቅት ስለርሳቸው ያነበቧቸውን ደጋግና መልካም ነገሮች ሲያጋሩ እናንተ ሂዳችሁ ትገጅራላችሁ?
አለይሰ ኢንደኩም አቅል??
ይሄ ነገር ሂዶ ሂዶ ወደ ነብያችን ጥላቻ እንዳያድግባችሁ ብትጠነቀቁ መልካም ነው። እልህ መጥፎ ነው። ከብዙ ሀቆች ያስፈነግጣል። ዛሬ ላይ የተወለዱበትን ወርና ቀን የማስጠላት አዝማሚያ እያሳያችሁ መሆኑን ገለልተኛ ሆኖ የሚያችሁ የሚያረጋግጠው ሀቅ ነው። በወሩ ውስጥ የነብያችንን ስም ማንሳት ራሱ እንደት እንደሚያንዘረዝራችሁ ሳይ ይአጅበኛል!
አላህ ስክነቱን ይስጣችሁ። ሰከን ብላችሁ ብታስተነትኑ ይሄን ያክል እርቀት የሚያስኬድ ጥላቻ ውስጥ የሚያስገባችሁ አንዳችም ነገር አልነበረም።
ለኡማው መፈራረቅና ከውጭም ለሚመለከተው አካላ ያሉብን ስንጥቆሽ አጉልቶ የሚያሳይ ነገር ነው።
በኢልምና መነጋገር ፣ በአሊሞች መመካከር የሚፈታን ፊቂሀዊ ጉዳይ የአደባባይ አጀንዳ አድርጋችሁ መሰረታዊ የሚባል የኢልም እርሾን እንኳ ሳትይዙ ሙስሊም ባልሆኑ ወገኖቻችን ገፅ ሁሉ እየሄዳችሁ ፈትዋ የምትሰጡ ሰዎች ሀቂቃ ታሸማቅቃላችሁ!
ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

110
20
17
3
3
3
1
1August 26, 2026 6.8K 119 9