የነብዩን ሱና ለመከተል ብላችሁ ነው አይደል? ነብያችንን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ስለምትወዱ ነው አይደል? በቃ… — Seid Social — TG.ME

የነብዩን ሱና ለመከተል ብላችሁ ነው አይደል? ነብያችንን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ስለምትወዱ ነው አይደል?
በቃ አትሳደቡ!
ጋጠወጥ ንግግር አትናገሩ!
እንዴ የምትሳደቡት ስድብ የምትናገሩት ንግግርኮ እንኳን ዲነኛ ከሆነ ሰው ይቅርና ጥሩ ወላጅ ካሳደገው ሰውም አይጠበቅም!

የናንተን ስድብ የናንተን የባህሪ ብልሽት የሚመለከት ሰው ኢስላምን በምን መልኩ ሊመለከተው ይችላል ብላችሁ አታስቡም?

ነብያችንን የሚከተል በፍፁም ተሳዳቢ አነዋሪ አንቋሻሽ አይሆንም!
የመልካም ስነምግባር ዝቅጠት የኢማን መድከም ምልክት እንጅ የጀግንነት አይደለም።

ሶሻል ሚዲያ ላይ ስለተሳደባችሁ ነውረኛ ንግግር ስለተናገራችሁ ጀግና የሆናችሁ ያክል የሚሰማችሁ አዲመል አኽላቆች እረፉ!
ሰው አዛ አታድርጉ!
በናንተ ስድብ የሚስተካከል ነገር የለም።
የኢልምና አደብ እጥረት ምን አይነት ትውልድ እየፈጠረብን ነው በአላህ!

ማክቨሩንም መራገሙንም መሳደቡንም ከኢስላም ማስወጣቱንም ማንም ሪከርዱን አይስበርብን የሚል ሩጫ ላይ ናችሁ!

በቃ ኢማነኛ ናችሁ አ ለራሳችሁ ተኩራሩበት። ሌላውን አዛ አታድርጉ! ጀነት ስለምትገቡበት እንጅ ሌላው ጀሀነም እንደት ይግባልን እያላችሁ አትጨነቁ!

"በጀነት ሙሽራዎች" እዳችንን አየንኮ!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
👍87❤54🥴14👏7🤔5🫡2🥰1
August 25, 2026 7.3K 60 9