ሕይወቴን ያደፈረሰው ምስጢር! ክፍል 19 ከአሮጊቷ ቤት ከተመለስኩ በኋላ በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች በሙሉ… — 🌔የቀልብ ዶክተር🌔 طبيب القلب📿 — TG.ME

ሕይወቴን ያደፈረሰው ምስጢር!

ክፍል 19
ከአሮጊቷ ቤት ከተመለስኩ በኋላ በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች በሙሉ በጥቅትና በጥርጣሬ ማየት ጀመርኩ። የቅርብ ጓደኛዬ ፋጡማ ጎረቤታችን እመቤት፣ አበበች ሌላው ቀርቶ የመንደሩ ሰዎች በሙሉ በእኔ ላይ ሴራ የሚያሴሩ ይመስሉኝ ጀመር።
እናቴ አጠገቤ መጥታ ውኃ ስትሰጠኝ እንኳ «ምናልባት ውኃው ውስጥ የሆነ ነገር አድርጋበት ይሆን?» ብዬ እጠራጠር ነበር። ይህ ጥርጣሬ አእምሮዬን በከፍተኛ ሁኔታ አበላሸው። ሰዎችን መጥላትና ከሰዎች መራቅ ጀመርኩ።
በክፍሌ ውስጥ ሆኜ በሩን እቆልፍ ነበር እናቴና አባቴ እንኳ ወደ ውስጥ እንዲገቡ አልፈቅድም ነበር። «ማንንም አላምንም! ሁላችሁም ልትጎዱኝ ትፈልጋላችሁ!» ብዬ እጮህ ነበር። እናቴ በበሩ ውጭ ሆና ታለቅስ ትማፀነኝ ነበር።
በዚህ ሁኔታ በቤታችን ውስጥ ያለው ፍቅርና እምነት ሙሉ በሙሉ ጠፋ። ሁላችንም በጥርጣሬና በፍርሃት ታሰርን። አባቴም ከእኔ ጋር ማውራት አቆመ እናቴም ተስፋ አጣች። በዚያች ምሽት በክፍሌ ውስጥ ብቻዬን ሳለሁ የባሰው ነገር ተከሰተ...
ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ በክፍሌ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ጨለማ ነበር። እኔ በመሬት ላይ ተኝቼ እንቅልፍ እንቢ ብሎኝ ጨንቆኝ እያለቀስኩ ሳለሁ በክፍሉ ማዕዘን ውስጥ አንድ ሰው በሹክሹክታ የሚያወራ ያህል ድምፅ ተሰማ። ድምፁ በጣም ቀርቦ ነበር ልክ በጆሮዬ አቅራቢያ እንደሚናገር ሰው።
«ማንም ሊረዳሽ አይችልም ወላጆችሽ እንኳ ጠልተውሻል። አሁን ብቻሽን ነሽ!» አለ ድምፁ። ያን ጊዜ በልቤ ውስጥ ያለው ተስፋ ሙሉ በሙሉ ተሰበረ። «አዎ... ብቻዬን ነኝ» ብዬ አሰብኩ።
ዕንባዬ በጉንጮቼ ላይ ይፈስ ነበር በሰውነቴ ላይ ያለው ሕመም ግን አልቆመም። አየር ለማግኘት እታገል ነበር ደረቴም በከባድ ጫና ተወጥሮ ነበር። «ያ አላህ! ለምን አልሞትም? ለምን ይህ ሁሉ ስቃይ ይደርስብኛል?» ብዬ በታላቅ ሀዘን ጮህኩ።
የእኔ ጩኸት እናቴን አባነናት። እናቴ በሩን ገፍትራ ገባችና እኔን አቅፋ ማልቀስ ጀመረች። «ልጄ... አይዞሽ እኔ አጠገብሽ ነኝ» አለች። ነገር ግን የእናቴ እቅፍ እንኳ በውስጤ ያለውን ስቃይ ሊያቆመው አልቻለም። በዚያች ምሽት፣ ሕይወቴ ወደ ሁለተኛውና የባሰው የፈተና ምዕራፍ ተሸጋገረች...


#ፈጥነው_ይታከሙ_በቶሎ_ይዳኑ

🔸አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው🔸

💡💡لا غالبَ إلا الله💡💡

💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇

⭐️     https://t.me/Qallbdoc


ህክምና ለማግኘት👇

https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇

https://t.me/UstazulQallb

👆

ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇

📱 https://qalebdoctor.com
❤13😢3👍1
September 6, 2026 990 4