ክፍል 15
በማግስቱ ጠዋት ገና ማለዳ በጭጋግ የተሸፈነችውን መንደራችንን ጥለን ወደ ከተማው ለመሄድ ተነሳን። አባቴ አንድ አሮጌ ጋሪ ተከራይቶ በዛውም ወደ ምንሄድበት ቦታ ጋሪውን ሊያደርስለት ተስማምቶ ነበር፡፡
እኔና እናቴ በጋሪው ላይ ተቀመጥን። የመንደሩ መንገድ ባዶ ነበር ነገር ግን በጥቂት ቤቶች መስኮቶች በኩል ሰዎች እኛን ሲመለከቱ አያለሁ። አብዛኞቹ በሀዘንና በጭንቅት ስጋት ይመለከቱናል፡፡ አንዳንዶቹ ግን ከእኛ ጋር ላለመገናኘት ጀርባ ይሰጡ ነበር።
ጋሪው ወደፊት ሲጓዝ የትውልድ መንደሬ ከዓይኔ እየራቀች ሄደች። «ምን አልባት ዳግመኛ አልመለስም ይሆን?» የሚል ከባድ ሀዘን ልቤን ወረረው። በጉዞው ላይ አባቴ ምንም አላወራም ነበር፡፡ እጆቹን አጣጥፎ ወደ መሬት ያይ ነበር። እናቴ ደግሞ በእጇ ያለውን የሙስበሃ ፍሬዎች እያነሳች አላህን ታስታውስ ነበር።
የፀሐይ ብርሃን በደመናው መካከል ለመውጣት ሲታገል ይታያል ነገር ግን በእኔ አእምሮ ውስጥ ያለው ጨለማ ሊገፈፍ አልቻለም። የከተማው መንገድ እየተቃረበ በመጣ ቁጥር በውስጤ ያለው ጭንቀት እየጨመረ ሄደ።
ከተማው ስንደርስ የቃጭልና የተሽከርካሪዎች የትላክስ ድምፅ ጭንቅላቴን አዞረው። በርካታ ሰዎች ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ይሮጣሉ የንግድ ቦታዎችና ረጅም ህንፃዎች አካባቢውን ሞልተውታል። ለእኔ ይህ ሁሉ አዲስና አስፈሪ ነበር። አባቴ እጄን አጥብቆ ይዞ ወደ አንድ ትንሽ ክሊኒክ አመራን፡፡
ጤና ጣብያው በሰዎች ተሞልቶ ነበር። የሕመምተኞች ማልቀስና የህክምና ዕቃዎች ሽታ አእምሮዬን በጭንቀት ወጥሮታል። እኛም ተራችንን ጠብቀን ወደ ሀኪሙ ክፍል ገባን። ሀኪሙ ወጣትና የሰለጠነ ይመስል ነበር ነጭ ልብሱን ለብሶ በ ፈገግታ ተቀበለን።
አባቴ የነበረውን ሁኔታ በዝርዝር አስረዳው። «ልጄ በድንገት ተቀየረች አትበላም አትተኛም በሌሊት ትጮሃለች ደግሞም በውስጧ የተለየ ነገር አለ» አለ። ሀኪሙ በአክብሮት ካዳመጠ በኋላ እኔን የመመርመሪያ አልጋ ላይ እንድጋደም አዘዘኝ።
የደም ግፊቴን የልብ ምቴንና የደሜን ናሙና ወስደው መረመሩኝ። ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመጠቀም የአእምሮዬንና የሰውነቴን ሁኔታ መረመሩ። ከሁለት ሰዓት ጥበቃ በኋላ ሀኪሙ ውጤቱን ይዞ ወደ እኛ መጣ።
«አባት የልጅህ ደም የልብ ምትና የአእምሮ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ጤናማ ነው። ምንም ዓይነት አካላዊ ወይም አእምሮአዊ በሽታ አላገኘንባትም» አለ ሀኪሙ። አባቴ በመገረም «እንዴት ጤናማ ትሆናለች? እጃችን ላይ እያለቀሰችኮ ነው!» አለ። ሀኪሙም «በእኛ የህክምና እውቀት ምንም አይነት በሽታ የለባትም ምናልባት የስነ-ልቦና ጫና ይሆናል» ብሎ መለሰ። ያን ጊዜ አባቴና እናቴ እርስ በእርሳቸው አጉረመረሙ ነገሩ ከህክምና ቁጥጥር ውጭ እንደሆነ አረጋገጡ..
#ፈጥነው_ይታከሙ_በቶሎ_ይዳኑ
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere
👆
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb
👆
ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇

