ክፍል 16
ከጤና ጣብያው ከተመለስን በኋላ አባቴ ተስፋ ሳይቆርጥ ወደ ሌላ ቦታ ሊወስደኝ አሰበ። በከተማው ዳርቻ የሚገኝ አንድ በባህላዊና መንፈሳዊ ሕክምና ይታወቃል የተባለ ሰው ዘንድ ወሰደኝ። ያ ቦታ በርካታ ታማሚዎች ተሰብስበው የሚጠብቁበት ትልቅ ግቢ ነበር።
ሰዎቹ በተለያዩ መንገዶች ያቃሰቱና ይጮሁ ነበር አንዳንዶቹ ታስረው ነበር። ያን ቦታ ስመለከት በውስጤ ታላቅ ፍርሃት ተፈጠረ። «እኔም እንደ እነዚህ ሰዎች ልሆን ነው?» ብዬ አሰብኩ።
ወደ ሕክምናው ክፍል ስንገባ ሕክምና ሰጪው የተባለው ሰው የተለያዩ የቅጠል ጭማቂዎችንና የተቀመሙ ዘይቶችን አወጣ። በእጆቼና በፊቴ ላይ ያን ዘይት እየቀባ በርካታ ድምፆችን ማውጣት ጀመረ። ነገር ግን ያን ዘይት በተቀባሁ ቁጥር በቆዳዬ ላይ እንደ እሳት የሚቃጠል ሕመም ይሰማኝ ጀመር።
«ያቃጥለኛል! አቁሙ!» ብዬ ጮህኩ። አባቴ እጆቼን ይዞ «ታገሺ ልጄ መድኃኒቱ ነው» አለኝ። ነገር ግን ያ ሕክምና ምንም ዓይነት እፎይታ አልሰጠኝም፤ይልቁንም ሕመሜንና ጭንቀቴን በእጥፍ አበዛው። በዚያች ምሽት ወደ አደደርንበት ትንሽ እንደ ማረፍያ ተደርጋ ወደ ተሰራች መጠለያ ከተመለስን በኋላ የባሰ አደጋ ተከሰተ፡፡
ያደርንበት ክፍል ትንሽና ጨለማ ነበረች። እናቴና አባቴ በድካም ምክንያት በፍጥነት እንቅልፍ ወሰዳቸው። እኔ ግን በጀርባዬ ተንጋልዬ በሕመም አቃሰት ነበር። በሰውነቴ ላይ የተቀባው ዘይት አሁንም ያቃጥለኝ ነበር።
ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ገደማ የክፍሉ በር በራሱ ጊዜ ተከፈተ። ምንም ዓይነት ነፋስ አልነበረም ነገር ግን በሩ በቀስታ ተከፈተ። በበሩ በኩል አንድ ግዙፍና ጥቁር ጥላ ወደ ክፍሉ ገባ። ያ ጥላ የሰው ቅርፅ ነበረው ነገር ግን ፊቱ አይታይም ።
ጥላው ወደ እኔ አልጋ እየቀረበ መጣ። ለመጮህ ሞከርኩ ነገር ግን ድምፄ ሙሉ በሙሉ ጠፋ። ጥላው እጆቹን ወደ አንገቴ አቀረበ መተንፈስ አቀተኝ። አየር ለማግኘት እጆቼን እያውለበለብኩ ታገልኩ።
በዚያ ቅጽበት በእናቴ እጅ ላይ ያለው የመስበሃ ፍሬ ወለሉ ላይ ወድቆ ተበተነ። ድምፁ አባቴን አባነነው። አባቴ በፍጥነት መብራቱን አበራ። መብራቱ ሲበራ ጥላው በቅስፈት ጠፋ እኔ ግን አየር ለማግኘት እየታገልኩ መሬት ላይ ተደፍቼ ነበር።
ይህ ሁሉ የሆነው በህልምሽ ነው ቢሉኝም የሙስባሃው መሰበር በእውን ቢሆንም ለኔ ግን ሁሉም እውን ነበር፡፡ በኔ ጩሀትና ትንፋሽ ማጠር በሙስበሃው መበተን በርግጎ የተነሳው አባቴ ደንግጦ ወደ እኔ ሮጠ...
#ፈጥነው_ይታከሙ_በቶሎ_ይዳኑ
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere
👆
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb
👆
ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇

