وَلَا تَحَاضُّونَ عَلَىٰ طَعَامِ الْمِسْكِينِ ١٨
وَتَأْكُلُونَ التُّرَاثَ أَكْلًا لَّمًّا ١٩
وَتُحِبُّونَ الْمَالَ حُبًّا جَمًّا ٢٠
በፍጹም እንዲህ አይደለም! የቲሙን አታከብሩም።
ድሃን ለመመገብም እርስ በርሳችሁ አትበረታቱም።
ውርስንም ሁሉን በማካተት ትበላላችሁ።
ገንዘብንም እጅግ በጣም ትወዳላችሁ።
መልክቱ
አላህ በእነዚህ አንቀጾች የመካ ከሓዲዎችን ባህሪ ይገልጻል። ሀብት ቢኖራቸውም የቲሞችን መብት አይጠብቁም ነበር፤ ድሆችንም ለመመገብ አይበረታቱም ነበር። እንዲሁም የሌሎችን ውርስ በግፍ ይበሉ ነበር፤ ገንዘብንም ከመጠን በላይ ይወዱ ነበር።
ትምህርቱ
የቲሞችን መብት መጠበቅ ያስፈልጋል።
ድሆችን መመገብና ሌሎችንም በዚህ ላይ ማበረታታት ይገባል።
በውርስ ጉዳይ ፍትሕን መጠበቅ ግዴታ ነው።
ገንዘብ ልብን እንዳይቆጣጠር መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
⭐️ https://t.me/Qallbdoc
✨https://t.me/dr_of_heart


