ክፍል 14
ያ አስፈሪ ድምፅ በሌሊቱ ጸጥታ ውስጥ ሲያስተጋባ የደም ስሮቼ በሙሉ የቀዘቀዙ ያህል ተሰማኝ። «አንቺ የእኛ ነሽ!» የሚለው ቃል በአእምሮዬ ውስጥ ይደጋገም ነበር። ከአልጋዬ ተነስቼ ወደ ክፍሉ ማዕዘን ተሸሸግኩ። ዓይኖቼን ጨፍኛቸው አላህን ማሰብ ፈለግኩ ነገር ግን አእምሮዬ የታሰረ ያህል ምንም ዓይነት ዚክር ማሰብ አልቻልኩም ነበር።
ያ ምስል ከመስኮቱ ውጭ ሆኖ ይስቅ ነበር የሳቁ ድምፅ የሸይጣን ድምፅ ነው ብዬ የማስበውን ይመስል ነበር። «ወደ አዋቂዎች ብትሄጂም ወደ ሀኪም ብትሄጂም መፍትሔ አታገኚም ሕይወትሽ በእኛ እጅ ናት» አለኝ። እኔም በደከመ ድምፅ «አላህ ከእናንተ በላይ ነው!» ብዬ ለመናገር ሞከርኩ።
ያን ጊዜ ያ ምስል በቁጣ ተሞልቶ የመስኮቱን የድሮ እንጨት በኃይል መታው። እንጨቶቹ ተሰብሮ ወደ ውስጥ ወደቀ። ከየት መጣ ሳልለው እኔ ደግሞ ነስር ጀመረኝ ደሜ በወለሉ ላይ ተሰራጨ። እናቴና አባቴ የድምፁን መከሰት ሰምተው በሩን በርግደው ወደ ውስጥ ገቡ።
ክፍሌ ውስጥ ሲገቡ እኔ በደሜ ተነክሬ መሬት ላይ ተጥዬ አገኙኝ። እናቴ ጮኻ ወደ እኔ ሮጠች። አባቴ ግን በመስኮቱ ስብርባሪዎችና በእኔ ሁኔታ ደንግጦ ቆሞ ነበር። «ይህ ነገር ከቁጥጥራችን ውጭ ሆኗል!» ሲል አባቴ በፍርሃት ድምፅ ተናገረ፡፡
ከዚያ አደጋ በኋላ አባቴና እናቴ አንገቴን ወደላይ ከፍ አስደርገውልኝ ደሜ መቆሙን አረጋገጡ ነገር ግን በቤታችን ውስጥ ያለው ፍርሃት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ። አባቴ «ነገ ወደ ከተማ እንወስዳታለን እዚያ ያሉ ሀኪሞችንና የሃይማኖት አባቶችን ኡስታዞችን እንጠይቃለን» አለ።
እናቴ አጠገቤ ተቀምጣ እጆቼን እየዳበሰች ታለቅስ ነበር። «ልጄ ይህ ሁሉ ስቃይ ለምን በ አንቺ ላይ እንደመጣ አላውቅም ነገር ግን አላህ አይጥለንም» አለች። የ እናቴ ጥቂት የጽናት ቃላት በልቤ ውስጥ ትንሽ የተስፋ ጭረት ፈጠሩ።
ነገር ግን በዚያች ምሽት አባቴና እናቴ ውጭ ተቀምጠው ሲያንሾካሹኩ ሰማሁ። አባቴ «ይህ ነገር ተራ ሕመም አይደለም የሆነ ሰው በ እሷ ላይ ሲህር አድርጎባታል ወይ ደሞ መንፈስ መቷታል» ሲል ሰማሁ። «ሲህር» የሚለውን ቃል ስሰማ ደሜ በቅዝቃዜ ተሞላ።
ከዚህ ቀደም «ሲህር» የሚለውን ቃል በጥቂቱ ሰምቼ ነበር፡፡ ነገር ግን በእኔ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ጨርሶ አስቤ አላውቅም ነበር። «በእርግጥ በእኔ ላይ ሲህር ተደርጎብኛል ወይንስ የአእምሮ ሕመም ነው?» ብዬ ራሴን ጠየቅኩ። ያን ጊዜ ግን ከደጃፋችን ውጭ የተሰማው ያ ያልተለመደ የሴት ሳቅ የሕይወቴ ሁለተኛውና የባሰው ጨለማ ክፍል ሊጀምር እንደሆነ አበሰረኝ...
#ፈጥነው_ይታከሙ_በቶሎ_ይዳኑ
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere
👆
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb
👆
ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇


