ክፍል 10
በማግስቱ ጠዋት አባቴ በከፍተኛ ሀዘንና ቁጣ ወደ ቤት ተመለሰ። ልብሱ በጭቃ ተለውሶ ነበር፡፡ ፊቱም ላይ ትልቅ ድካምና ሀዘን ይታይበት ነበር። እናቴ ደንግጣ «ምን አጋጠመህ አባቱ?» ስትል ጠየቀችው። አባቴ ወንበር ላይ ተቀመጠና እጆቹን ጭንቅላቱ ላይ ጭኖ «ሰብላችን በሙሉ ወድሟል ሌሊቱን ሙሉ ያልተጠበቀ ትልና በሽታ እህሉን በልቶታል አንበጣ ይሁን አይጥ ይሁን በሙሉ ጠቁሯል » አለ።
ይህ ለእኛ ቤተሰብ ትልቅ ውድቀት ነበር። ያ ሰብል የዓመቱ ሙሉ የኑሮ ምንጫችንና የልብስ የምግብና የቤተሰብ ወጪ መሸፈኛችን ነበር። አባቴ «ይህ ተፈጥሯዊ ነገር አይደለም በአንድ ሌሊት ሙሉ የእርሻ መሬት እንዴት ይወድማል?» እያለ ይበሳጭ ነበር። እናቴም ደንግጣ ማልቀስ ጀመረች።
እኔ በበኩሌ በሩ አቅራቢያ ቆሜ ይህን ሁሉ ስመለከት በውስጤ ትልቅ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። ምክንያቱም ይህ ሁሉ መከራ ወደ ቤታችን የገባቸው በእኔ ላይ እንግዳ ነገሮች መታየት ከጀመሩ በኋላ ነበር። «አላህ ሆይ! በ እኔ ምክንያት ቤተሰቤን አትቀጣ» ብዬ በውስጤ ተማፀንኩ።
አባቴ ወደ እኔ ዞሮ ተመለከተኝ። በዓይኖቹ ውስጥ የቀደመው ፍቅር አልነበረም በጣም ነበር የሚወደኝ ያኔ ግን ይልቁንም ጥርጣሬና የከበደ ስጋት ይታይ ነበር ፊቱ ላይ። «ከዚህች ልጅ ጋር የሆነ ነገር አለ እሷ ወደ ቤታችን መጥፎ ነገር አምጥታለች» ብሎ ሲናገር ልቤ በጠርሙስ ቁራጮች የተበጫጨቀ ያህል ተሰማኝ። እናቴም አባቴን ለመቃወም አቅም አጣች፡፡
ከእርሻችን ውድመት በኋላ በቤታችን ውስጥ ያለው ሁኔታ እጅግ የከፋ ሆነ። የገንዘብ እጥረት የምግብ እጥረትና የሀዘን ሸክም ቤታችንን ወረረው። አባቴ በየቀኑ ከቤት ወጥቶ እስከ ምሽት አይመለስም ነበር ሲመለስም በትንሽ ነገር ይቆጣ ነበር። ታናሽ ወንድሜም ከእኔ ጋር ማውራት አቆመ በእኔ ላይ የሆነ ያልተለመደ ነገር እንዳለ ስለተነገረው መሰለኝ ጭራሽ ይፈራኝ ጀመር።
እኔ በራሴ ክፍሌ ውስጥ ተዘጋሁ። በቀን ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ የመሳልፈው በጨለማ ነበር። ምግብ የመብላት ፍላጎቴ ሙሉ በሙሉ ጠፋ ሰውነቴ ከቀን ወደ ቀን እየከሰመና እየደከመ ሄደ። መስታወት ውስጥ ስመለከት የራሴን ፊት ማመን አቃተኝ። ዓይኖቼ ስር ጥቁር ነገር ወጥቶ ነበር እንደ ማድያት፡፡ ቆዳዬም ብርሃኑን አጥቶ ነበር እንዳረጀች ሴት አይኔ እምባ በእምባ ሆና አነሰችብኝ።
አንድ ቀን እናቴ ወደ ክፍሌ ገብታ አቅፋኝ አለቀሰች። «ልጄ... ምን እየሆነብሽ ነው? እባክሽን አንድ ነገር ተናገሪ ይሄን ሆኛለሁ በይኝ» አለችኝ። እናቴን አቅፌ ማልቀስ ፈለግኩ ነገር ግን ዕንባዬ ድርቅ ብሎ ነበር። «እማ እኔም አላውቅም... በውስጤ የሆነ ነገር እየተቃጠለ ነው ደስ የማይል ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ ውስጤ ድብርት አለ ይጨንቀኛል ያመኛል» ብዬ መለስኩላት።
እናቴም «ነገ ወደ መስጂዱ ኢማም ቤት እንወስድሻለን እሳቸው ቁርአን ቀርተውልሽ መፍትሔ ያገኙልሻል» አለችኝ። የቁርአን ስም ሲነሳ በውስጤ አንድ ዓይነት ጭንቀትና ፍርሃት ተፈጠረ። ለመሄድ ፍላጎት አልነበረኝም ነገር ግን የእናቴን ጥያቄ ላለመቃወም ስል እሺ አልኩ። ሆኖም ግን ወደ ኢማሙ ለመሄድ በታቀደበት ቀን ሌላ ያልተጠበቀ ክስተት ተከሰተ...
#ፈጥነው_ይታከሙ_በቶሎ_ይዳኑ
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere
👆
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb
👆
ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇


