የተፈጥሮአዊን ስኳር እና ደም ግፊት በሽታ በሲህር ከሚከሰተው ስኳርና ደም ግፊት የሚለዩ ምልክቶች! ‼️… — 🌔የቀልብ ዶክተር🌔 طبيب القلب📿 — TG.ME

‼️ የተፈጥሮአዊን ስኳር እና ደም ግፊት በሽታ በሲህር ከሚከሰተው ስኳርና ደም ግፊት የሚለዩ ምልክቶች! ‼️

🖍(በኡስታዛህ ዶ/ር ኡሙ ረያን)

​ብዙ ጊዜ ታካሚዎቼ "የተፈጥሮን እና የሲህርን ህመም እንዴት እንለያለን?" ብለው ይጠይቁኛል። ያየነውን ምልክት ሁሉ "ሲህር ነው" ብሎ መደምደም ተገቢ አይደለም። ለምሳሌ እድሜዋ በሃምሳዎች ውስጥ የሆነችና በቤተሰቧ የስኳር ታሪክ ያላት ሴት ብትታመም፣ ይህን ወደ ሲህር መውሰድ ስህተት ነው።
​በሌላ በኩል ግን፣ ምንም አይነት አጋላጭ ምክንያት (Risk factor) የሌለውን ሰው ድንገት በሽታው ሲያጠቃው ዝም ብሎ ማለፍም አይገባም። ሲህር፣ ጅንና አይነናስ እነዚህን በሽታዎች ሊያመጡ ይችላሉ። ልዩነታቸውን በሚከተሉት 7 ምልክቶች እንለያለን፦

ክፍል 1

1 ​ #የድንገት_ስኳር ወይም የደም መጠን ከፍ ማለት፡- ምግብ ከተበላ በኋላ የስኳር መጠን መጨመሩ ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ በረሃብ ስሜት ላይ እያሉ፤ እንዲሁም ምንም አይነት የስኳር ህመም ምልክቶች (ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት፣ ማጠማት) ሳይታዩ ድንገት ስኳርዎ ከሚባለው በላይ ከፍ የሚል ከሆነ የሲህር ምልክት ሊሆን ይችላል።

2 ​ #ቀላል_እንዳይሆን_ያረገው_እድሜን ያላማከለ መሆኑና እድሜያቸው ከ40 አመት በታች ሲሆኑ፡- ዓይነት 2 (Type
2) የስኳር ህመም በአብዛኛው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑትን ያጠቃል። ነገር ግን ምንም አጋላጭ ምክንያት ሳይኖር ከ40 ዓመት በታች ያሉ ሰዎችን ድንገት ይህ ህመም ቢያጠቃቸው፣ ከሲህር የመጣ ሊሆን እንደሚችል እንጠረጥራለን።

3​ #ልክ_በመሃል_ሶስት ቀን ወይም አራት ቀን ቆይቶ ጥፍት ማለት፡- ለሶስት ቀናት ያህል የስኳር ህመም ምልክቶች (ቶሎ ቶሎ ማሸናት፣ ማስጠማት) አሳይቶና በሆስፒታል ስኳር ተብሎ፣ ወዲያው በአራተኛው ቀን ሙሉ በሙሉ ጤነኛ መሆንና ሲመረመርም ከደማችን ውስጥ የስኳር ምልክት መጥፋት። ይህ ሲህሩ አዲስ (ትኩስ) ደረጃ ላይ እንዳለ ያሳያል።

4 ​ #ብርቱ_የሆድ ጩሀት፡- ሌሎች የስኳር ምልክቶች እየታዩዎት፣ በተጨማሪም ሆድዎ ያለአንዳች ምክንያት በጣም የሚጮህና አውሬ እንደሚንቀሳቀስበት አይነት የሚረብሽ ከሆነ፤ ስኳሩ ከሲህር የመጣ ሊሆን እንደሚችል ማገናዘብ ይኖርብዎታል።

5​ #ዶሮ_ከነጥሬዋ_የሚያስውጥ በሃይል የመራብ ከረሃብ ኋላና ፊት የሰውነት መንዘፍዘፍ፡- በተፈጥሮ ስኳር ህመም ወቅት ረሃብና መንዘፍዘፍ ቢኖርም፣ የሲህር ሲሆን ግን ረሃቡ ጉልበት ያለው፣ ወደ አውሬነት የሚቀይር፣ እጅግ የሚያናድድና የሚያስቆጣ ይሆናል። ሰውነትን በከፍተኛ ትኩሳት የሚያሳልብና የሚያንቀጠቅጥ ከሆነ ሲህር ብቻ ሳይሆን ጅኑም ጉልበቱን እንደዘረጋ ያሳያል።

6 ​ #ክፉነቱ_ምሽት_ብቻ_ጠብቆ የደም ከፍ ማለት ጫንቃ መጨምደድ፡- የደም ግፊትዎ ምሽትን ብቻ ጠብቆ ጫንቃዎን የሚጨመድድዎ ከሆነ፤ ክሊኒክ ሲለኩ ከፍተኛ ሆኖ ጠዋት ሲነሱ ግን ሙሉ በሙሉ ሰላም ከሆኑ፤ ምግብም ሆነ ቡና ሲወስዱ የማይጨምር ከሆነ፣ ይህ የሲህር ምልክት ሊሆን ይችላል።

7 ​ #ተራ_አይደለም_ደም ከፍ ሲል መተንፈስ አለመቻል ያመጣል፡- የሲህር ደም ግፊት ዋነኛ መለያ ትንፋሽ ማጠር ነው። ደም ግፊቱ ከፍ ሲል ልክ እንደ አስም ታካሚ መተንፈስ ያቅትዎታል፣ ትንፋሽዎ ይቆራረጣል። ይህ ስሜት ጠዋት ሊጠፋ ወይም ላይጠፋ ይችላል፤ የደም ግፊት መድሃኒት ቢወስዱም እንኳን በቀላሉ አይስተካከልም።

8​ #ርእሱ_ላይ_ካለው_ህመም ወይም ከዚህ አይነት ሲህሮች በአላህ ኃይል እንጠበቃለን።

ማንኛውም አይነት አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ ህመሞች ሲገጥሙዎት፤ በኢስላማዊ እውቀት ብቁ የሆኑ የሩቅያ ዶክተሮችን፣ የሜዲካል ዶክተሮችን እና የሳይካትሪስት ባለሙያዎችን ለማግኘት ወደ "ቀልብ ዶክተር" ቻናል ያምሩ። ህክምናዎን በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) መንገድ ያግኙ። ለሁላችሁም ከልብ አፊያን ተመኘሁ፣ ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ!!

​#ሲህር #ስኳር_በሽታ #ደም_ግፊት #ሩቅያ #ጅን #ቀልብ_ዶክተር #ኢስላማዊ_ህክምና #ፈውስ #ኡስታዛህ_ኡሙ_ረያን #ጤና #አይነናስ


አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው
🔸

💡💡لا غالبَ إلا الله💡💡

💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇

⭐️ https://t.me/Qallbdoc


ህክምና ለማግኘት👇

✈️https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇

✈️https://t.me/UstazulQallb

👆

ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇

📱 https://qalebdoctor.com
❤5👍3
August 28, 2026 1.1K 7