Orthodoxy: post #847 — TG.ME

ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

ለሳምራዊቷ ሴት የተሰጠ ለዘለዓለም የማያስጠማ የሕይወት ውሃ ክርስቶስ ነው። የምንኖረው በእርሱ ነው ፤ የምንወርሰው መንግስታችንም እርሱ ነው። እርሱ በእኛ እኛም በእርሱ እንኖር ዘንድ ቃሉን ከፈጸምን /ሥጋውን ከበላን/ ቃሉን ይፈጽም ዘንድ የታመነ ነው።

ፍጹም እውነት እና ሕይወት ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ወንጌላችን እርሱ ነው። ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ ይሁን ወንጌል የለንም። የምናምነው የምንሰብከው ወንጌላችን ፤ የምንሞትለት አምላካችን እርሱ ክርስቶስ ነው። ለሚጠሩት ስሙ ጣፋጭ ፣ ለሚጠጡት ለዘለዓለም የማያስጠማ የሕይወት ውሃ ፣ ለሚበሉት ለዘለዓለም የማያስርብ የሕይወት ምግብ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው።

ፍጥረት ሁሉ የሚሰግዱለት የሆነው ሁሉ በእርሱ የሆነ ፤ ከሆነውስ እንኳ አንዳንች እንኳ ያለ እርሱ የሆነ ነገር የሌለ ፤ በሥጋ የተገለጠ ፣ በጥቂቱ ያደገ ፣ ለፍጥረቱ ሁሉ ሕይወትን የሰጠ ፣ አዳምን ከብልየት ያዳነው ፤ በመስቀል በፍቃዱ ስለ እኛ የሞተ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

ከእርሱ በቀር ሌላ ስበከት የለም ፤ ከእርሱም በቀር ሌላ ትምህክት የለንም። ወንጌላችን እርሱ ሕይወታችንም አምላካችንም እርሱ ነው።

የሕግ ፍጻሜ ፍቅር መሆኑን በሥጋ ተገልጦ በመስቀል ከዚህ የበለጠ ፍቅር ለማንም የለውም የተባለውን የፈጸመ ፤ እንዲሁ የወደደን አምላካችን እርሱ ክርስቶስ ነው።

ይኼን ስም ለዓለም ለዘለዓለም እንሰብካለን።

#orthodoxy
🥰1
July 24, 2026 203