አዕምሮህ ጋሻ ወይስ የገሃዱ ዓለም እንቅፋት?
ሳይንቲስቶች በአንድ ወቅት አንድ አስደናቂ ሙከራ አድርገው ነበር።
በአንድ ትልቅ የዓሣ ማርቢያ ገንዳ ውስጥ በመካከል ላይ ግልጽ የሆነ የብርጭቆ መክፈያ ግድግዳ አደረጉ። በአንዱ በኩል የተራበ እና ኃይለኛ አዳኝ የሆነ “ፓይክ” (pike) የተባለ ዓሣ፣ በሌላኛው በኩል ደግሞ ትናንሽ ዓሳዎችን አስቀመጡ።
ፓይኩ ታዳኝ አሳዎቹን ባየ ቅጽበት በከፍተኛ ፍጥነት ይወረወራል፤ ነገር ግን በቀጥታ የማይታየው የብርጭቆ ግድግዳ ላይ ይጋጫል። ደጋግሞ ይሞክራል፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ጥቃት በተመሳሳይ ውድቀት ይጠናቀቃል። ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ፣ አካሉ የዛለውና የደከመው ፓይክ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጦ ወደ አንዱ ጥግ ያፈገፍጋል።
በመቀጠል ሳይንቲስቶቹ ያንን የብርጭቆ መክፈያ ግድግዳ በቀስታ ያነሱታል።
አሁን ትናንሾቹ ዓሳዎች በፓይኩ ፊት ለፊት በነጻነት ይዋኛሉ፤ እሱ ግን ዳግመኛ ሊያ'ድናቸው አልሞከረም። በጣም እየተራበ ቢሆንም እንኳን ምግቡን ችላ ብሎ ተኛ።
ምክንያቱም እውነተኛው ጋሻ ወይም ከለላ ከእንግዲህ ብርጭቆው አልነበረም፤ በአዕምሮው ውስጥ የታሰረው “አልችልም” የሚለው እምነቱ እንጂ!
ከቀናት በኋላ፣ ያ ፓይክ በምግብ ተከቦ እያለ በረሃብ ሞተ።
የአዕምሮ እንቅፋት (Mental Barrier) ኃይል እንግዲህ ይህ ነው!
ብዙዎቻችን ዛሬ የምንኖረው ልክ እንደዚህ ዓሣ ነው። ትናንት የገጠመን አንድ ውድቀት ወይም ያጣነው እድል፣ ዛሬም ስኬት የማይቻል መሆኑን ያሳምነናል።
ነገር ግን ልብ በል፦ ትናንት የከለከለህ መሰናክል ዛሬ ላይኖር ይችላል! የከበበህ ብርጭቆ ተነስቷል።
ነገሮች ተቀይረዋል፤ አንተም ተቀይረሃል። ስለዚህ እጅ ከመስጠትህ በፊት አንድ ጊዜ ደግመህ ሞክር! የሚቀጥለው ሙከራህ ሁሉንም ነገር የሚቀይር፣ ታሪክህን የሚያድስ ሊሆን ይችላል።
Source psych addis
https://t.me/mrtababl
Telegram
የሳይኮሎጂ ምክሮች
🔥ድንቅ አዝናኝና አስተማሪ አባባሎች
🔥የሳይኮሎጂ ምክሮችን ለማግኘት
ይቀላቀሉ

19
7
2July 20, 2026 2.3K 10