🤐ድክም
ለምን እንደሆነ ባላቅም ድክም አለኝ ። ለምን አትበሉኝ ግን ስሙ ግራ ሚያጋባ ስሜት ብቻ መቅረት : ከሰው ጋር ሆነህ አለመታየት ; የፈለከውን አለማድረግ ;የሚያመጣው ስሜት ብቻ ስሙን ምን ልበለው ተስፋ መቁረጥ ወይስ ተስፋ ማጣት ? በሁለቱ መሀል ሆኖ መኖር ባልፈልገውም ያደክማል ። ያልፋል እኮ ግን አደከመኝ የኔ በምትላቸው ሰው ተረግጦ መኖር ለችግሩ የደረስክለት ሰው በችግርህ ሲደበር ማየት እና መነሳት አለመቻል ያደክማል ። ድካሜ ሲብስብኝ የሌለኝን ባህሪ መላበስ እየጀመርኩ ነው ነገ ለሚነጋው ዛሬን የለበሱትን ጭንብል አውልቀው እኔ ላይ ማንነታቸውን ለማሳየት ከሞከሩት ጋር አስተዛዘበኝ ግን ለበጎ ነው ብስሉን ከጥሬው መለየቴ ። ፌክ ማንነትን ስግብግብነትን ሳልፈልግ እናንተው አውርሳቹኛ ነገር ግን እራሳቹ የሰጣቹኝን ማንነት እራሳቹ ላይ ሳንፀባርቀው እንዳይደብራቹ ። ግን ላሁኑ ደክሞኛል ✌️😔
🥺ከተወዛገበቺዋ ሂወት የተገኘ
✍ አሚኮ