ከእለታት በ....
የተስፍ ጠዋቶችን ኖራለች፤ የሀዘን ለሊቶችንም አልፍለች የመወደድን ሙቀት አውቃለች ፤ የመረሳትንም ዝምታ ተምራለች።
ጊዜ ሊያጠፍቸው የማይችሉትን ስህተቶች ሰርታለች ፤ማጣት ያልፈለገቻቸውን ሰዎች አታለች ፤ ሌላ ሰው ሊያያቸው የማይችላቸውን ቁስሎች በውስጧ ተሸክማለች።
አንዳንድ አመታት ድል ሰተዋታል
ሌሎች ግን መፅናናት ብቻ አስተምረዋታል
ምላልባት ሰዎች ያልተረዱት ይህን ነው...
እያንዳንዱ የስኬት አመት ድል መሆን የለበትም አንዳንድ አመታት የመትረፍ ምዕራፎች ብቻ ናቸው። እነዚያን አመታት አላባከናቸውም።
ተሰምተዋታል
ተሸክማለች
ተምራለችም
በውስጧ አድጓል
ራሷንም በነዚያ አመታት ውስጥ ሆና ኖራለች
ተምሬበታለው
ኖሬበታለሁ...
እና አንዳንድ ጊዜ ሂወት ከናንተ ብዙ ነገር ከወሰደች በኃላ እስከ መጨራሻው መኖራቹ እራሱ ትልቁ ድል ሊሆን ይችላል ።
#s✍
@semhalyaa





