የሳይኮሎጂ ምክሮች: post #882 — TG.ME

የአንተ ህይወት ዋና ተዋናይ ማነው?

ብዙዎቻችን ህይወታችንን እንዲያስተካክልልን፣ ካለንበት ‘ጭንቅ’ ውስጥ እንዲያወጣን ወይም “ተነስ” ብሎ ፍቃድ እንዲሰጠን የምንጠብቀው አካል አለ። ወላጆቻችን፣ የትዳር አጋራችን፣ አልያም ድንገት የሚመጣ “እድል”።

ሳይኮሎጂ የሚነግረን ግን እውነታው ሌላ መሆኑን ነው።

እውነታው ይህ ነው፦

ማንም መጥቶ ህይወትህን ሊያስተካክልልህ አይችልም። ማንም!

ካለህበት ሁኔታ “ነጻ” ሊያወጣህ የሚችል ምልክት ወይም ሰው አትጠብቅ።

ያንተን ሁኔታ ሊለውጠው የሚችለው አንተ ራስህ ብቻ ነህ።

ዛሬ የምናደንቃቸው እና የደረሱበት ቦታ የደረሱ ሰዎች “ሁሉ ነገሬ ተሟልቷል፣ ዝግጁ ነኝ” ብለው አልጀመሩም።

እንዴት ጀመሩ መሰለህ?

እየፈሩ፣ እርግጠኛ ሳይሆኑ፣ ባዶ እጃቸውን እያሉ፣ እና በራሳቸው እየተጠራጠሩም ቢሆን ያኔ ባላቸው አቅም መጓዝ ጀመሩ።

ዛሬ አንተም መወሰን አለብህ፦ ዝግጁ እስክትሆን መጠበቅ ትፈልጋለህ ወይስ በጥርጣሬ ውስጥ ሆነህ እርምጃ መውሰድ?

ምርጫው ያንተው ነው!

Source psych addis
❤12🔥3
August 14, 2026 1.4K 5